ለምንድነው የሚንኖረው
Lemendenew Yemenenorew
4:51 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰው ሰው የሆነበት የሚኖርበት ምክንያት ካልገባው
በአካል ኖረ እንጂ የነፍሱን ክፍተት በምን ሊሞላው
ኑሮን ለማሸነፍ እሮጦ እሮጦ ቢደርስ ከግቡ
ተሳካለት ቢባል ሃሳቡ ሞልቶ እንዲያው ለደንቡ
ግን ይሄ አይደለም የሕይወት ትርጉሙ
ከማግኘት ይበልጣል ለተፈለጉበት መገኘት በውሉ
ሃብትን ለማካበት ከመባዘን ይልቅ
ለምን እንደምንኖር በተጋን ለማወቅ
አዝማች · Chorus
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እርካታ በገንዘብ በመብል መጠጥ ከተገደበ
በጉብዝናው ጊዜ የፈጠረውን ሰው ካላሰበ
ኋላ በእድሜው ምሽት እንዳይጸጸት ከአሁኑ ይንቃ
የተፈለገበትን ምክንያት ያግኝ ቀኑ ሳያበቃ
በምድር ላይ ያስገኘን በሰማያት ያለ
አላማ ሰጥቶናል የምንኖርብት ከቁስ በዘለለ
ሁሉም በየድርሻው በተሰጠው ስራ
ለመፈጸም ይሩጥ የአምላክን አደራ
አዝማች · Chorus
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰው ሰው የሆነበት የሚኖርበት ምክንያት ካልገባው
በአካል ኖረ እንጂ የነፍሱን ክፍተት በምን ሊሞላው
ኑሮን ለማሸነፍ እሮጦ እሮጦ ቢደርስ ከግቡ
ተሳካለት ቢባል ሃሳቡ ሞልቶ እንዲያው ለደንቡ
ግን ይሄ አይደለም የሕይወት ትርጉሙ
ከማግኘት ይበልጣል ለተፈለጉበት መገኘት በውሉ
ሃብትን ለማካበት ከመባዘን ይልቅ
ለምን እንደምንኖር በተጋን ለማወቅ
አዝማች · Chorus
ለምንድነው የምንኖረው
እስትንፋሳችን የሚቀጥለው
ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ
ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ