ተሰሚ ነህ
Tesemi Neh
5:08 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተሰሚ ነህ በሰማይ በምድር
ጉልበት ሁሉ ሚንበረከክልህ
የፈጠርከን እንሰግድልሃለን
ሞገስህን ክብርህን እያየን
ይሹሩን ሆይ በሰማያት ላይ ለእረድኤትህ
በደመናት ላይ እንደሚሄድ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ቁጥር 1 · Verse 1
ኧረ እንደርሱ ያለ ቢፈለግም የለም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘመንህ ዘላለም ከቶ አታረጅም
አምሳያ የለህም መቼም አትተካም
አዬዬ መቼም አትተካም
ፊትህ እንደ ፀሐይ በሀይል የሚያበራ
ከዋክብት ጨረቃን ደመናን የሰራህ
አዬዬ ፀሐይን የሰራህ
የአማልክቱ አምላካቸው ነህ
የፍጥረት ገዢ የዓለማት ንጉሥ ነህ
ወሰን የሌለህ ስራህ እረቂቅ
የማትታወቅ የሆንህ እጅግ ታላቅ
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ ታላቅ አምላክ የለም
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ አይኖርም ዘላለም
አዝማች · Chorus
ተሰሚ ነህ በሰማይ በምድር
ጉልበት ሁሉ ሚንበረከክልህ
የፈጠርከን እንሰግድልሃለን
ሞገስህን ክብርህን እያየን
ይሹሩን ሆይ በሰማያት ላይ ለእረድኤትህ
በደመናት ላይ እንደሚሄድ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ቁጥር 3 · Verse 3
እንደርሱ ያለ ቢፈለግም የለም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የዓለም ሁሉ መሪ ብርቱ ነህ ሀይለኛ
ከሁሉ ቀዳሚ የሌለህ ፊተኛ
አዬዬ የሌለህ ፊተኛ
ይሁን ባልከው ቃልህ ሁሉ ተፈጠረ
እቅድህ ግሩም ነው ስራህም ያማረ
አዬዬ ስራህም ያማረ
የአማልክቱ አምላካቸው ነህ
የፍጥረት ገዢ የዓለማት ንጉሥ ነህ
ወሰን የሌለህ ስራህ እረቂቅ
የማትታወቅ የሆንህ እጅግ ታላቅ
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ ታላቅ አምላክ የለም
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ አይኖርም ዘላለም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ