ፍቅር ነው ለእኔ
Feqer New Lenie
2012 · ትራክ 5 · 6:16 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለእኔ ከላይ ከሰማይ (፪x)
መሞት የሚገባኝ ነበርኩ
መጣልኝ ሲሳይ
አዝማች · Chorus
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ ምንም/አንዳች የለ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከላይ ከሰማይ የባሪያን መልክ ይዞ
በእኔ በኃጢአተኛዋ በፍቅር ተይዞ
ካለሁበት: አዘቅት ከሞት ሊያወጣኝ
እርሱ ዋጋ ከፍሎ ነጻ ነሽ አለኝ
አዝማች · Chorus
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ ምንም/አንዳች የለ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በዚያ በጐልጐታ በቀራኒዮ ላይ
ከቶ መች አፈረ እርቃኑ ሲታይ
የህማም ሰው ሆነ ተመታ በደዌ
እርሱ ዋጋ ከፍሎ ይኸው ዳንኩኝ
አዝማች · Chorus
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ ምንም/አንዳች የለ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ወርዱና ስፋቱ የማይለካው
ጥልቅ ነው ፍቅሩ ወሰን የሌለው
የልቤ አይወጣም ብዙ ቃል ደርድሬ
ሳመሰግን ብውል በመልካም ዝማሬ
ለእኔ ከላይ ከሰማይ (፪x)
መሞት የሚገባኝ ነበርኩ
መጣልኝ ሲሳይ
አዝማች · Chorus
ፍቅር ፍቅር ፍቅር
ፍቅር ነው ለእኔ
እንደዚህ የሚያደርገው
ከእኔ ምንም/አንዳች የለ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ