ሕይወቴን ፈውስ
Hiwotien Fewes
2012 · ትራክ 2 · 4:44 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ብላቴና ሳለሁ የመረጥከኝ አምላክ
ለአንተ እንድዘምር ታማኝ አርገህ ቆጥረህ
በሁለንተናዬ እንዳከብርህ አንተን
ፀጋህን አብዛልኝ ፈውሰው ሕይወቴን
አዝማች · Chorus
እባክህ ኢየሱስ (፪x) ሕይወቴን ፈውስ/ቀይር
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰዎች እኔን ሲያዩ ስምህ እንዲቀደስ/እንዲከበር (፪x)
እባክህ ባክህ እግዚአብሔር
ሕይወቴን ቀይር
ሕይወቴን ቀይር
እባክህ
ሕዝብህን ልትባርከው ስትሰጠኝ ፀጋ
ከትላንቱ ይልቅ ወደ አንተ ልጠጋ
ለታይታ አይሁን መንፈሳዊነቴ
አንተን እንዲገልጥህ መላው እኔነቴ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ አባቴ (፪x) ክበር በሕይወቴ
ቁጥር 3 · Verse 3
በሁሉ ይገለጥ የሕይወት እድገቴ
ስለእኔ ኃጢአት ደምህ ፈሶልኛል
እራስህን ሰውተህ ሕያው አድርገኸኛል
እኔ ግን ለአንተ መኖር ተስኖኛል
እጅህ ግን ከመጣ አድኖ ያስቀረኛል
አዝማች · Chorus
እባክህ ኢየሱስ (፪x) ሕይወቴን ቀድስ
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተን ለተራቡ ቃልህን እንዳለ
ሕያውና ቅዱስ መስዋዕት አድርጌ
ለአንተ ሰውነቴን እንዳቀርብ አምላኬ
በፍፁም መለወጥ ሕይወቴ ይገራ
በዘመኔ ሁሉ አንተን እንድፈራ
አዝማች · Chorus
እባክህ እግዚአብሔር (፪x) ሕይወቴን ቀይር
ቁጥር 5 · Verse 5
ደግሞም መጨረሻዬ በፊትህ እንዲያምር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ