Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተወለድ እንደገና

Tewelede Endegena

2012 · ትራክ 9 · 4:24 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሕይወት ጐዳና ተስፋ ቆርጦ ሞትን ለሚጠብቀው

እረፍትን ፍለጋ ተቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው

ኢየሱስ ነው መፍትሄው

ኢየሱስ ነው ሚያድነው (፪x)

በራስህ ኃይልና ጉልበት ነፍስህን አታድንም

በያዝከው ሃብትና ንብረት እርካታን አታገኝም

ይልቅስ ቶሎ ብለህ : ና ትምክትህን ተውና

ኢየሱስ ጌታዬ ብለህ ተወለድ እንደገና

ያኔ ነው እርካታህ

ያኔ ነው ፍፁም ደስታህ (፪x)

በሕይወት ጐዳና ተስፋ ቆርጦ ሞትን ለሚጠብቀው

እረፍትን ፍለጋ ተቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው

ኢየሱስ ነው መፍትሄው

ኢየሱስ ነው ሚያድነው (፪x)

በመስቀል ላይ ጌታ ሲሞት እዳህን ተሸክሞ

ከኃጢአት ደዌ ሊያድንህ ስለአንተ እርሱ ቆስሎ

ኃጢአትህን ደምስሶልሃል ንጹህ ደሙን አፍስሶ

ና ልጄ ናና ይልሃል ስራህንም ጨርሶ

ድምጹን ስማ ወዳጄ ተከፍቷል የምህረት ደጄ

ድምጹን ስማ ወዳጄ ተከፍቷል የምህረት ደጄ

በሕይወት ጐዳና ተስፋ ቆርጦ ሞትን ለሚጠብቀው

እረፍትን ፍለጋ ተቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው

ኢየሱስ ነው መፍትሄው

ኢየሱስ ነው ሚያድነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ