ላይተወኝ ቃል ገብቶአል
Laytewegn Qal Gebtual
2012 · ትራክ 7 · 4:50 · አማርኛ
ያላዩት አገር አይናፍቅም እንደሚሉት ሰዎች
ተረት አይደለም ዓይኔ አይቶት ነው የልቦናዬ
ሕይወቴን እንካ ኑሮዬን እንካ ብዬ የሰጠሁት ለዚህ ጌታዬ
ዛሬም ፍቅሩ ያዘኝ
ምህረቱ ያዘኝ
ፀጋው ያዘኝ
ያዘኝ (፭x)
ያዘኝ (፬x)
ላይተወኝ ቃል ገብቷል ላይጥለኝ
የጌታዬ ፍቅሩ ማረከኝ (፪x)
ሰላሙን ሞላ በቤቴ
ተለወጠልኝ ሕይወቴ
በቀኙ ደግፎ ያዘኝ
መንፈሱ አሳረፈኝ
አሁን አሁንማ (አሁንማ)
ለሌላው አተረፈኝ
ኢየሱስ ደረሰልኝ (፪x)
ልዑል መጠጊያ ሆነኝ በክንፉ አሳረፈኝ
ልቤ ከሥጋት አረፈ ጽዋዬ እየተረፈ (፪x)
አሁን አሁንማ (አሁንማ)
ለሌላው አተረፈኝ
ኢየሱስ ደረሰልኝ (፪x)
በጠላቶቼ ፊት ለፊት ቀባኝ አምላኬ በዘይት
ገመዴ ባማረ ስፍራ ወደቀች/ወድቃለች ልቤ እንዳይፈራ (፪x)
አሁን አሁንማ (አሁንማ)
ለሌላው አተረፈኝ
ኢየሱስ ደረሰልኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ