Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አይዞህ

Ayzoh

2012 · ትራክ 6 · 5:13 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ነገን ነገን ስታይ ቢጨልምብህ/ከጨልምብህ

በተስፋ ተራመድ እራዕይ ይኑርህ/አለህ (፪x)

አይዞህ (፫x)

ሥራ ብታጣ ገንዘብ ቢጠፋ

ቢጨልምብህ አይዞህ

ሚረዳህ አጥተህ ብቻህን ብትሆን

ተስፋ ባይኖርህ አይዞህ (፪x)

አስሩን ስታስብ ሚሰማህ እንዳነስህ

ከሁሉ የበታች የሆንክ የመሰለህ

አይዞህ (፫x)

ልዩ የሆነ ችሎታ አለህ

ተነስ ታገል አይዞህ

ከማንም አታንስ ይኸው ራስህም

ብቃት እኮ አለህ አይዞህ

መስራት ማችልበት ምንም ምክኒያት የለ

ጠንክረህ ብትሰራ ብዙ ታጭዳለህ

አይዞህ (፫x)

የረፈደብህ እየመሰልህ

ትተክዛለህ አይዞህ

በዚህ ጉብዝናህ በሙሉ ኃይልህ

መራመድ ጀምር አይዞህ

አንድ ቀን ያልፋል (፫x)

የወደደ ያከበረ ያፈቀረ

አምላክ አለህ አለህ

የወደደ ያፈቀረ ያከበረ

አምላክ አለህ አለህ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ