Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አማላጄ

Amalajie

2012 · ትራክ 13 · 3:17 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በቅድሚያ ነብያት የተናገሩለት

ስለእርሱ ሚያወራ መጽሐፉ ቢገለጥ

እግዚአብሔርም አለ ልጄ እርሱ ነው ስሙት

እናቱ ማርያምም ሚላችሁን አድምጡ

አማላጄ ኢየሱሴ ነው (፬x)

ኢየሱሴ ነው ፤ ኢየሱሴ ነው (፬x)

ሌሎች ፍጥረታቶች አማላጅ ሚባሉ

እስቲ እንያቸው መስቀል ላይ ከዋሉ

በቀራኒዮ መስቀል የሞተው ስለእኛ

ኢየሱስ ብቻ ነው የሰው ልጅ መዳኛ

አማላጄ ኢየሱሴ ነው (፬x)

ኢየሱሴ ነው ፤ ኢየሱሴ ነው (፪x)

እውነትና ሕይወት ሰላም መንገድ ነኝ ያለው

በእርሱ በቀር ወደአብ ሚሄድ ኧረ እስቲ ማነው

እግዚአብሔር አብ የሰውን ልጅ ይጠራዋልና

በሚያድነው በኢየሱስ ይዳን ይመንና

ይዳን ይመንና (፬x)

በቅድሚያ ነብያት የተናገሩለት

ስለእርሱ ሚያወራ መጽሐፉ ቢገለጥ

እግዚአብሔርም አለ ልጄ እርሱ ነው ስሙት

እናቱ ማርያምም ሚላችሁን አድምጡ

አማላጄ ኢየሱሴ ነው (፬x)

ኢየሱሴ ነው ፤ ኢየሱሴ ነው (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ