Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከአንተ የሚበልጥ

Kante Yemibelt

ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከአንተ የሚበልጥ ለእኔ ማንም የለም

አንተ ብቻ አምላኬ/አንደኛ ዘለዓለም

ዘለዓለም ተባረክልኝ ዘለዓለም ተወደስልኝ

ዘለዓለም ተባረክልኝ ዘለዓለም ተወደስልኝ (፪x)

በሕይወቴ ዘመን አመሰግናለሁ

በአንተ ሥም እጆቼን የእኔ ጌታ አምላኬ አነሳለሁ

በቅበና በስብ እንደሚጠግቡት የእኔ ጌታ

ነፍሴ ትጠግባለች አምላኬ ያልኩትን

ከአንተ የሚበልጥ ለእኔ ማንም የለም

አንተ ብቻ አንደኛ ዘለዓለም

ዘለዓለም ተባረክልኝ ዘለዓለም ተወደስልኝ

ዘለዓለም ተባረክልኝ ዘለዓለም ተወደስልኝ

ቅዱሳኑ ሁሉ እርሱን ወደዱት የእኔን ጌታ

ፊተኛ ቀዳሚ ሆሆ አንደኛ አድርጉት ሆ

አንተ ስትወደድ እጅግ ደስ ይለኛል የእኔ ጌታ

የወዳጄ ወዳጅ ልቤን ያረካኛል

ከአንተ የሚበልጥ ለእኔ ማንም የለም

አንተ ብቻ አንደኛ ዘለዓለም

ዘለዓለም ተባረክልኝ ዘለዓለም ተወደስልኝ

ዘለዓለም ተባረክልኝ ዘለዓለም ተወደስልኝ

ክብር ይሁን ክብር

ክብር ይሁን ምሥጋና

በጽድቅ የተሞላህ ሆሆ

ድንቅ አምላክ ነህና (፪x)

ክብር ይሁን ክብር

ክብር ይሁን አምልኮ

በጽድቅ የተሞላህ ሆሆ

ድንቅ አምላክ ነህኮ (፪x)

ላመልክህ እወዳለሁ

ላመልክህ እወዳለሁ

ላመልክህ እወዳለሁ ላመልክህ (፪x)

ላከብርህ እወዳለሁ

ላከብርህ እወዳለሁ

ላከብርህ እወዳለሁ ላከብርህ

እስትንፋስ ያላቸው ፍጥረታት ሁሉ

እንዴት አንተን አይተው እንዴት ዝም ይላሉ

በቋንቋቸው ሁሉም ያመሰግናሉ

ክብር ለአንተ ይሁን ተመሥገን ይላሉ

ክብር ይሁን ክብር

ክብር ይሁን ምሥጋና

በጽድቅ የተሞላህ ሆሆ

ድንቅ አምላክ ነህና (፬x)

ከክብርም በላይ በላይ ይሁንልህ

ከምሥጋና በላይ በላይ ይሁንልህ ይሁንልህ

ይሁንልህ ይሁንልህ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ