እንደ እግዚአብሔር ያለ
Ende Egziabhier Yale Yelem
ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ባወራው አያልቅም ቸርነቱ
ፍቅሩ ርህራሄው ምህረቱ (፫x)
አላያችሁም ዎይ ሁሉን ቻይነቱን
ፍቅሩን ምህረቱን ደግሞም ደግነቱን
አልሰማችሁም ዎይ እግዚአብሔርነቱን
ሰለቸርነቱ ሰለምህረቱ
አዝማች · Chorus
እንደ እግዚአብሔር ያለ ሆሆ
እንደ አምላኬ ያለ ሃሃ
እደነቃለሁኝ ሆሆ
በምድር ስለሌለ ሃሃ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከሰው ልጆች መሀል የሚመስልህ የለም የለም
ከፍጥረታት መሃል የሚመስልህ የለም
ከአማልክት መሃል የሚመስልህ የለም የለም
አንተ ብቻህን ነህ አምላኬ ዘለዓለም
እርሱ ብቻ ብቻውን ነው (፪x)
ጅማሬና ፍጻሜ የለውም ፣ ፍጻሜ የለው
አንተ ብቻ ብቻህን ነህ (፪x)
ጅማሬና ፍጻሜ የለህም ፣ ፍጻሜ የለህ
አዝማች · Chorus
እንደ እግዚአብሔር ያለ ሆሆ
እንደ አምላኬ ያለ ሃሃ
እደነቃለሁኝ ሆሆ
በምድር ስለሌለ ሃሃ
ቁጥር 3 · Verse 3
አምላኬን የሚተካከልው ማነው
ጌታዬን የሚስተካከልው ማነው
ኦ እደነቃለሁ (፫x)
እኔ እደነቃለሁ (፫x)
አዝማች · Chorus
እንደ እግዚአብሔር ያለ ሆሆ
እንደ አምላኬ ያለ ሃሃ
እደነቃለሁኝ ሆሆ
በምድር ስለሌለ ሃሃ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ