ሥራዬ አንተን ማምለክ ነው
Serayie Anten Mamlek New
ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሥራዬን ሰራለሁ
ሥራዬም አንተን ማምለክ ነው
ሥራዬም አንተን ማምለክ ነው (፪x)
ሥራቸው ምንድን ነው
የእኔ ግን እርሱን ማምለክ ነው (፪x)
በየጠዋቱ በየማታው
መክብር መወደስ የሚገባው
አላስገደደኝ አላዘዘኝ
እኔ እራሴ ፈቃደኛ ነኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሥራዬን ሰራለሁ
ሥራዬም አንተን ማምለክ ነው (፪x)
ሥራዬን ሰራለሁ
ሥራዬም አንተን ማክብር ነው (፪x)
ሥራዬን ሰራለሁ
ሥራዬም ለአንተ ማዜም ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አላጓድልም ሥራዬን
አንተን ማምልኬን ማክብሬን
አላጓድልም ሥራዬን
መውደዴን ማፍቀሬን
ነጋልኝ ደግሞ ላመስግነው
ምሥጋናዬ ለጌታዬ ይድረሰው
እስኪመሽ እስኪጨልም ድረስ
አምልኮዬ በዙፋኑ ይፍሰስ (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ ሆሆ የእኔ ወዳጅ
የእኔ ንጉሥ የእኔ ወዳጅ
የእኔ ጌታ የእኔ ወዳጅ
የእኔ ንጉሥ የእኔ ወዳጅ
ነጋልኝ ደግሞ ላመስግነው
ምሥጋናዬ ለጌታዬ ይድረሰው
እስኪመሽ እስኪጨልም ድረስ
አምልኮዬ በዙፋኑ ይፍሰስ
ቁጥር 4 · Verse 4
ያለመጠን ያለልክ አመሰግንሃልሁ አመሰግንሃልሁ (፪x)
ልክ አለኝ ልክ አለኝ ገደብን አውቃለሁ
አንተን ለማምልክ ግን ገደቤን ጥሻለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ ሆሆ የእኔ ወዳጅ
የእኔ ንጉሥ የእኔ ወዳጅ
የእኔ ጌታ የእኔ ወዳጅ
የእኔ ንጉሥ የእኔ ወዳጅ
ነጋልኝ ደግሞ ላመስግነው
ምሥጋናዬ ለጌታዬ ይድረሰው
እስኪመሽ እስኪጨልም ድረስ
አምልኮዬ በዙፋኑ ይፍሰስ
ቁጥር 5 · Verse 5
እንደሚያበራ እንደሚደምቅ እንደ ከዋክብት ነህ (፪x)
እንደምን ብዬ እንዴትስ ብዬ እንደምን ላድንቅህ (፪x)
በሚገባኝ ቋንቋ ባሞጋግስህ ከሚገባኝ በላይ አንተ ልዩ ነህ (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ ሆሆ የእኔ ወዳጅ
የእኔ ንጉሥ የእኔ ወዳጅ
የእኔ ጌታ የእኔ ወዳጅ
የእኔ ንጉሥ የእኔ ወዳጅ
ነጋልኝ ደግሞ ላመስግነው
ምሥጋናዬ ለጌታዬ ይድረሰው
እስኪመሽ እስኪጨልም ድረስ
አምልኮዬ በዙፋኑ ይፍሰስ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
እስኪመሽ እስኪጨልም ድረስ
አምልኮዬ በዙፋኑ ይፍሰስ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ