Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የልቤ አምላክ

Yelebie Amlak

ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ

የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፪x)

እንደ ጥል ሆንክልኝ እንደ አበባ አበብኩኝ

እንደ ሊባኖስ ስሬ በቤትህ ሥር ሰደድኩኝ

እንደ ወይራ ውበት እንደ መዓዛዉ

በእኔ ያስቀመጥከው ዓለምን ሞላዉ (፪x)

የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ

የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፪x)

እንደ ዘንባባ ዛፍ እያሳደገኝ

ፍሬዬን አበዛው አለመለመኝ

እንደ ረካች ገነት አምላኬ አደረገኝ

በብዛት በብዛት በብዛት ባርኮኝ

የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ

የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፪x)

እንደ ጠዋት ፀሐይ እንደሚያበራዉ

የጻድቃንም መንገድ እንደዚሁ ነዉ

ሙሉ ቀን እስኪሆን ገና ይጨምራል

የእኔም ዕድል ፈንታ እነሆ እንዲህ ሆኗል

የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ

የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፪x)

በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው አለ ወይ

የሥጋ ለባሽ አምላክ የሚያቅተው አለ ወይ (፪x)

ልቤ በእግዚአብሔር ጸና (፬x)

እርሱን ተማመነ ሆሆ እርሱን ተማመነ (፪x)

በውሃው ላይ እየተረማመደ እየተረማመደ

ለሚፈሩ እምነትን አስለመደ (፪x)

ማዕበሉም ወጀቡም የሚታዘዝለት

ይሄ ማነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው (፪x)

የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ

የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ