Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከእልፍ የተመረጠ

Keelf Yetemerete

2012 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ውዴ ከእልፍ የተመረጠ ነው

ከቶ ምን እርሱን ሊተካው

የሕይወትን ቃል አለው

ውስጤን ያሳረፈው የዘለዓለም አምባዬ ነው

የዘለዓለም ምርጫዬ ነው

የዘለዓለም አምባዬ ነው (፪x)

መናወጥ ከሞላበት የምጥ ዘመን

የእራሱ በቂ የሆነ ክፋት ያለበት

ነፍሴን ከሚያስጨንቅ ዕለት ዕለት

መኖሪያዬ ኢየሱስን የዘለዓለም ማለት

ውዴ ከእልፍ የተመረጠ ነው

ከቶ ምን እርሱን የሚተካው

የሕይወትን ቃል አለው

ውስጤን ያሳረፈው የዘለዓለም አምባዬ ነው

የዘለዓለም ምርጫዬ ነው

የዘለዓለም አምባዬ ነው (፪x)

እራሱን ሊገልጥ ወዶ ያደረገው

የሕይወት መንገድ ትግል የበዛው

ክፉዉን ለበጐ የለወጠው

አምላኬ በጥበቡ አሳመረው

ውዴ ከእልፍ የተመረጠ ነው

ከቶ ምን እርሱን የሚተካው

የሕይወትን ቃል አለው

ውስጤን ያሳረፈው የዘለዓለም አምባዬ ነው

የዘለዓለም ምርጫዬ ነው

የዘለዓለም አምባዬ ነው (፪x)

በማልመርጠው መንገድ ሲማራኝ

ለካስ ውዴ በሕይወት ሲጠብቀኝ

ልመናዬ ዝብዘባዬ ሳያውከው

መልካሙን ዘምን ለእኔ አቆየው

ውዴ ከእልፍ የተመረጠ ነው

ከቶ ምን እርሱን የሚተካው

የሕይወትን ቃል አለው

ውስጤን ያሳረፈው የዘለዓለም አምባዬ ነው

የዘለዓለም ምርጫዬ ነው

የዘለዓለም አምባዬ ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ