Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የሚበልጠው መንገድ

Yemibeltew Menged

2012 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሥራችንን ለእሳት መቃጠል አሳልፈን ብንሰጥም

በመልአክት ልሳን እንኳን ብንናገርም

ተራሮችን እስከናፈርስ እምነት ቢኖረንም

ፍቅር ግን ከሌለን ይህ ሁሉ አይጠቅምም

ከሁሉ የሚበልጠዉ መንገድ መንገድ

ፍቅር ነውና በእርሱ : እንሂድ (፪x)

አንዲያ ልጁን እስኪሰጠን ድረስ ከወደደን

በደላችንን ሳይቆጥር ከእራሱ ጋር ካስታረቀን

ከወንድማማች መዋደድ ነፍሳችንንም አጥተን

እንጓዝ ከሁሉ በሚበልጠው መንገድ እያስተዋልን

ከሁሉ የሚበልጠዉ መንገድ መንገድ

ፍቅር ነውና በእርሱ እንሂድ (፪x)

በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል

በእግዚአብሔርም በእርሱ ኑሮና ህይወት ይታያል

ጌታ ለእርሱ ያለውን ፍቅር ያወቀ ቢኖር

ባለ እንጀራውን እንደራሱ ይውደድ በደልን አይቁጠር

ከሁሉ የሚበልጠዉ መንገድ መንገድ

ፍቅር ነውና በእርሱ እንሂድ (፪x)

ዝቅ ዝቅ ማለትን መተጣጠብ ሲኖር

በፍቅር አንዱ ለሌላው እራሱን ማስገዛት ሲጀምር

አቤት የእግዚአብሔር ቤት ውበቱ ልዩ ነው መዓዛው

ፍቅር ነውና የርስቱ ዋና መለያው

ከሁሉ የሚበልጠዉ መንገድ መንገድ

ፍቅር ነውና በእርሱ እንሂድ (፪x)

ባለእንጀራችንን እንደ እራሳችን እንውደድ

ድካሙን እያየን በድፍረት አንፍረድ

እግዚአብሔር ፍቅር ነውና በፍቅር እንኑር

ይሄ ነው መታወቂያው የጌታ ደቀመዝሙር

ከሁሉ የሚበልጠዉ መንገድ መንገድ

ፍቅር ነውና በእርሱ እንሂድ (፪x)

ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር የሚረጋገጠው

በአጠገባችን ያለውን ወንድማችንን ስንወደው ነው

ጌታ ደስ በሎት መስዕዋታችንን የሚያሸተው

በደልን ይቅር የሚል ጥሩ ልብ ሲኖረን ነው

ከሁሉ የሚበልጠዉ መንገድ መንገድ

ፍቅር ነውና በእርሱ እንሂድ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ