እንደ ተሰጠህ አገልግል
Endeteseteh Agelgel
2012 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ደረት እየደቁ የተከተሉትን
"እናንተ የኢየሩሳሌም ሴቶች ለራሳችሁ አልቅሱ" ብሎ መልሶ
የተዘባበቱበትንም ሁሉ በመስቀል ላይ ጭምር ታግሶ
የመዳናችንም ራስ በመከራ የፈጸመውን ጌታ ተመልክተን
በተሰጠን ፀጋ በታማኝነት ለማገልገል እንበርታ
አዝማች · Chorus
እንደ ተሰጠህ አገልግል
ከሠማይ የሆነውን አደራ ችላ አትበል
ከሚያገሰግኑ አፍ እንዳትፈተን ልብህን አትጣ
በተቃዋሚዎችም ተደናግጠህ ፈቀቅ እንዳትል
የጠራህን ጌታ እያየህ ሩጫውን ቀጥል
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአፉ የሚወጣው ቃል ይሁን መኖሪያ
የተጻፈው ለትምህርት ይሁን መመሪያ
የላከህ ያለህን ሁሉ ያደረገ
ዳግመኛ ሲመለስ ጌታ እንዲያገኝህ
የጊዜው ስካር ከዓላማህ እንዳያስትህ
ንቃ ተጠበቅ አደራ እንዳያስጥል
አዝማች · Chorus
እንደ ተሰጠህ አገልግል
ከሠማይ የሆነውን አደራ ችላ አትበል
ከሚያገሰግኑ አፍ እንዳትፈተን ልብህን አትጣ
በተቃዋሚዎችም ተደናግጠህ ፈቀቅ እንዳትል
የጠራህን ጌታ እያየህ ሩጫውን ቀጥል
ቁጥር 3 · Verse 3
ዓለምን አትርፎ ነፍሱን ባያጐድል
ከአገለገለ በኋላ ራሱ እንዳይጣል
ሥጋውን እየጐሰመ ለጌታ ያስገዛል
እንጂ ራሱን መቼ ይሰብካል
አስተዋይ የማልጠቅም ባሪያ ንኝ ይላል
ክብርን ሁሌ ለጌታ ያስረክባል
አዝማች · Chorus
እንደ ተሰጠህ አገልግል
ከሠማይ የሆነውን አደራ ችላ አትበል
ከሚያገሰግኑ አፍ እንዳትፈተን ልብህን አትጣ
በተቃዋሚዎችም ተደናግጠህ ፈቀቅ እንዳትል
የጠራህን ጌታ እያየህ ሩጫውን ቀጥል
ቁጥር 4 · Verse 4
የልብሳቸውን ዘርፍ አስረዝመው አሸ. (1) . ሲያሰፉ
ጾመኛ መስለው ሊታዩ ለሰዎች ፊታቸውን ሲያጠፉ
አሥራት መጿት ሲያወጡ መለከት ሲያስነፉ
ግብዞች ልብን በሚያይ ጌታ . (2) .
የመንግሥቱ ሠማያት ደቀመዝሙር በእውንት ራሱን ይመርምር
አዝማች · Chorus
እንደ ተሰጠህ አገልግል
ከሠማይ የሆነውን አደራ ችላ አትበል
ከሚያገሰግኑ አፍ እንዳትፈተን ልብህን አትጣ
በተቃዋሚዎችም ተደናግጠህ ፈቀቅ እንዳትል
የጠራህን ጌታ እያየህ ሩጫውን ቀጥል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ