ፀሎቴን ቢከለክልም
Tselotien Bikelekelem
2012 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቢያሳዝንም እንደምሕረቱ ብዛት ይራራልና
የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅምና
አዝማች · Chorus
አፌን በአፈር ውስጥ 2x አኖራለው
ዝም ብዬ ማዳኑን ተስፋ አደርጋለው
እግዛብሄር የታመነ ነው 3x
ጌታዬ ለዘላለም አይጥልም
ቁጥር 2 · Verse 2
ጸሎቴን ቢከለክልም ጩህቴን ባይሰማ
ልመናን ሳበዛ ፊቱን ከእኔ ቢሰውርም
መንገዴን እስቲ ልመርምር
ወደ እግዛብሄር ልመለስ
ልቤን ከእጄ ጋር በሰማይ ወደለው ላንሳ
በሃጥያቴ ቢቆጣም እንኳ ስለዓመጻዬም ቢቀጣኝም
አዝማች · Chorus
እግዛብሄር መልካም ነው ፍጽሞ አይተወኝም
ከሰማይ እስኪጐበኘኝ እስኪመለከተኝ ድረስ
ዓይኔ ሳታቋርጥ እምባዬን ታፍስስ ታፍስስ
በጥቂት ቁጣ ፊቱን ከእኔ ቢሰውርም
በዘላለም ቸርነት ይምራል እግዚአብሔር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ