እግዚአብሔር ብቻውን
Egziabhier Bechawen
2012 · ትራክ 2 · 5:59 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ
በፀናች ክንድ በድል ረትቶ
የምታስፈራውን ምድረበዳ
ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ምደረበዳ
ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ
ቁጥር 1 · Verse 1
አማሌቅ በመንገድ ተቃወመን
ደክመን ሳለን መንገድ ዘጋጋብን
ተዋጊውእግዚአብሄር ድል አድርጎልን
ስንት ጭንቅ መንገዶችን አለፍን
ተዋጊው ወዳጄ ፊት ቀድሞልን
ስንት ጭንቅ መንገዶችን አለፍን
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ
በፀናች ክንድ በድል ረትቶ
የምታስፈራውን ምድረበዳ
ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ምደረበዳ
ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ
ቁጥር 2 · Verse 2
እርምጃችንን ሊያሰናክሉ የመከሩ
የክፋት ሰራዊት መጥመድን ሰወሩ
በመንገዳችን ላይ እንቅፋት አኖሩ
ጌታ ደርሶልን ፈረሰ ምክሩ (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ
በፀናች ክንድ በድል ረትቶ
የምታስፈራውን ምድረበዳ
ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ምደረበዳ
ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከአውሬ ጋር ብዙ ጊዜ ታግለናል
ስለነፍሳችን እንኳን ተስፋ ቆርጠናል
በብርቱ ሰልፍ መሀል ክንዱን አይተናል
በአምላካችን ብርታት ቅጥሩን ዘለናል (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ
በፀናች ክንድ በድል ረትቶ
የምታስፈራውን ምድረበዳ
ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ምደረበዳ
ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ
ቁጥር 4 · Verse 4
የጨካኞች ቁጣ እስትንፋስ
ቅጥርን እንደሚመታ አውሎንፋስ
ባየለበት ዘመን በእርሱ ድል አድርገናል
በክንዱ ፅናት ከሁሉ ተርፈናል (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ
በፀናች ክንድ በድል ረትቶ
የምታስፈራውን ምድረበዳ
ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ምደረበዳ
ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ