ላድንቅህ
Ladenekeh
ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የነፍሴ ቋንቋ ነህ (የሕይወቴ ዜና) ፪X
ማወደስ የማደንቅ (የአንተን ልእልና)፪X
የእኔ ተልእኮ ነው ጥሪና ውሳኔ
እስትንፋሴ እስካለች ቀሪውን ዘመኔ
ኢየሱስ ላድንቅህ ፬X
ቁጥር 1 · Verse 1
በፏፏቴው ውበት (እጆችህ ባበጁት)፪X
በተፈጥሮ ቀለም (ሁሉን ባቆነጁት)፪X
ግርምቴም አይበቃ (ዝም አይልም አፌ)፪X
ምሥጋና ይፈልቃል (ከመስክ ከደጃፌ)፪X
የተፈጠርኩበት የምድር ላይ ኑሮ
የተፃፈልኝም ሁሉም ተቀምሮ
አንተን ማወደስ ነው ክበር ክበር ማለት
ጅማረው ፊፃሜ (የሕይወቴ መሠረት)፪X
አዝማች · Chorus
የነፍሴ ቋንቋ ነህ (የሕይወቴ ዜና) ፪X
ማወደስ የማደንቅ (የአንተን ልእልና)፪X
የእኔ ተልእኮ ነው ጥሪና ውሳኔ
እስትንፋሴ እስካለች ቀሪውን ዘመኔ
ኢየሱስ ላድንቅህ ፬X
ቁጥር 2 · Verse 2
የሰማዩ ቀለም (የአድማሳቱ ግርማ)፪X
የንፋሱ ፉጨት (የአዋፋቱ ዜማ) ፪X
ክብርህን መናገር (ውዳሴን ማሳረግ)፪X
ዝናህን መተረክ (ከፍ ከፍ ማድረግ)፪X
የተፈጠርኩበት የምድር ላይ ኑሮ
የተፃፈልኝም ሁሉም ተቀምሮ
አንተን ማወደስ ነው ክበር ክበር ማለት
ጅማረው ፊፃሜ (የሕይወቴ መሠረት)፪X
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ