Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የሚመካ

Yemimka

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሥጋ ለባሽ ላይ የሚታመን

የተረገመ ነው እንደሚለው ቃሉ

በኢየሱስ ሚታመን አያፍርም አያፍርም ይላል ቃሉ

አንተን ተከትሎ የዳነ

ሰላሙ በዝቶለት እርፍ አለ

አስተማማኝ ጥላ ሆንከው

አይፈራ ሥጋት አያውቀው X፪

በጌታ ሚመካ ይመካ

በኢየሱስ ሚደገፍ ይደገፍ X፪

አይለዋወጥ እምነቴ

ጽኑ ነው በመድሃኒቴ

ዓይኖቼን ከሰው አንስቻለሁ

ቃሉ ሚለኝን አምናለሁ X፪

በጌታ ሚመካ ይመካ

በኢየሱስ ሚደገፍ ይደገፍ X፪

ያለኝን አምናለሁ ለምን እሰጋለሁ

ሰው እንኳን ተናግሮኝ ስንቱን አምኛለሁ

ሚያደርግ እንደ ቃሉ ሚፈጽም ሚተጋ

ጌታን በማመኔ አግኝቻለሁ ዋጋ

በጌታ ሚመካ ይመካ

በኢየሱስ ሚደገፍ ይደገፍ X፪

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ