ልዩ ነህ
Leyu Neh
ትራክ 4 · 4:09 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትላንት በጆሮዬ ከሰማሁት
ዓይኔም አይቶሃል
ልቤም ወዶሃል
ቁጥር 2 · Verse 2
ልዩ ነሃ X፪
ልዩ ነህ አሃሃ
ፍቅር ነህ አሃሃ
ልዩ አሃሃ
ፍቅር ነህ አሃሃ
ቁጥር 3 · Verse 3
ወዳጅ ሸቀጥ ሆኖ በገንዘብ ሲገዛ X፪
ለነገ ያስቀመጡት ሲናድ እንደዋዛ X፪
የእዳ ጽህፈቴ በዝቶ ሲከብደኝ X፪
በደሃ ጐጆዬ ገብተህ አየሁኝ
ኧረ እኔስ አየሁኝ
ኢየሱስ የአንተ እኮ ፍቅር ኧረ ይለያል
በቀንምም በማለዳም ያዘምረኛል X፪
አዝማች · Chorus
ልዩ ነህ አሃሃ
ፍቅር ነህ አሃሃ
ልዩ አሃሃ
ፍቅር ነህ አሃሃ
ቁጥር 4 · Verse 4
ለጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ተገኝቶ X፪
ሃጢውን ማን ይዋስ ከሰው መሃል ወጥቶ X፪
የእዳ ጽህፈቴ በዝቶ ሲከብደኝ X፪
ሕይወትን ሰጠኸኝ ቀርበህ ታደከኝ X፪
ብር ወርቅም አይደለም የፍቅር መለኪያህ
እንዲሁ መወደድህ ነው በደምህ አጥበህ X፪
አዝማች · Chorus
ልዩ ነህ አሃሃ
ፍቅር ነህ አሃሃ
ልዩ አሃሃ
ፍቅር ነህ አሃሃ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ