የረዳኝ
Yeredagn
ትራክ 3 · 4:23 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትላንት የረዳኝ ዛሬም ሚረዳኝ
ጌታን ይዣለሁ ምን አሰጋኝ X፪
አዝማች · Chorus
አለ ጌታ X፰
ቁጥር 2 · Verse 2
ባለፀጋው ኢየሱስ አባቴ
ምንጬ እኮ ነው በረከቴ
ከቶ አልሰጋም ምን እሆን ብዬ
እኖራለሁ ተዘልዬ X፪
ቁጥር 3 · Verse 3
መከራና ችግሩ ውጊያውም ቢበዛ
ድል አድራጊው ኢየሱስ አለ ከእኔ ጋራ
ያደርገዋል ጌታ የተናገረኝን
አየዋለሁ ይሆናል ቃል የገባልኝን
አዝማች · Chorus
ያለኝን ልመነው ልመነው ልመነው
ጌታዬ ታማኝ ነው ታማኝ ነው ታማኝ ነው X፪
ቁጥር 4 · Verse 4
ትላንት የረዳኝ ዛሬም ሚረዳኝ
ጌታን ይዣለሁ ምን አሰጋኝ X፪
አዝማች · Chorus
አለ ጌታ X፰
ቁጥር 5 · Verse 5
ቃሉን ሰጥቶ ያስጠበቀኝ
ከመንገድ ላይ መች ሊጥለኝ
እወርሳለሁ ጌታን ታምኜ
እሄዳለሁ ከእርሱ ጋር ሆኜ X፪
ቁጥር 6 · Verse 6
አባቶች አመኑት ደመናን ሳያዩ
ተስፋ እድርገው ጌታን ከቶ መች አፈሩ
በመጠበቂያዬ ላይ እጠብቀዋለሁ
ዘንበል ይላል ጌታ ቃሉን ምን ሊያደርገው
አዝማች · Chorus
ያለኝን ልመነው ልመነው ልመነው
ጌታዬ ታማኝ ነው ታማኝ ነው ታማኝ ነው X፪
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ