ማን አፈረ
Man Afere
ትራክ 6 · 3:58 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እስኪ ማን አፈረ አንተ ላይ ተማምኖ
ይባርክሃል እንጂ ክፉ ቀኑን አልፎ
ጭው ባለ ለሊት በሮች ተዘግተው
ኢየሱሴ ብሎ ያልዳነ ሰው ማነው
የእኔ እግዚአብሄር ጩኸትን የሚሰማ
የእኔ እግዚአብሄር እንባብ የሚያይ ነው
የእኔ እግዚአብሄር ከምድረበዳ ላይ
ምንጭ ያፈልቃል ያረካል ደርሶ ከላይ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምልክት ሳይኖት እድል ቀዳዳ
በንዳዱ እሳት በምድረበዳ
የሚያረሰርስ አፍልቆ ውኃ
የሚያለመልም ደረቅ በረሃ
አርክተህ ሁሉን ታስደንቃለህ
እንዲያው በመንገድ መች ትጥላለህ
የጉብኝት ቀን ሰጥተህ ቀጠሮ
ያልደረስክለት ማነው የሚኖር አፍሮ
ከቶ አልነበረም መቼም አይኖርም
ለተናገርከው ሳትደርስ አትቀርም
አዝማች · Chorus
እስኪ ማን አፈረ አንተ ላይ ተማምኖ
ይባርክሃል እንጂ ክፉ ቀኑን አልፎ
ጭው ባለ ለሊት በሮች ተዘግተው
ኢየሱሴ ብሎ ያልዳነ ሰው ማነው
የእኔ እግዚአብሄር ጩኸትን የሚሰማ
የእኔ እግዚአብሄር እንባብ የሚያይ ነው
የእኔ እግዚአብሄር ከምድረበዳ ላይ
ምንጭ ያፈልቃል ያረካል ደርሶ ከላይ
ቁጥር 2 · Verse 2
ማነው ጌታውን ያጣ ጠብቆ
ባዶ የቀረ የእጁን ተነጥቆ
ተተረከ እንጂ አባትነትህ
መች ተነገረ ቀጥረህ መቅረትህ
ጥበብ አይጎልህ ታስደንቃለህ
እንዲያው በመንገድ መች ትጥላለህ
የጉብኝት ቀን ሰጥተህ ቀጠሮ
ያልደረስክለት ማነው የሚኖር አፍሮ
ከቶ አልነበረም መቼም አይኖርም
ለተናገርከው ሳትደርስ አትቀርም
ቁጥር 3 · Verse 3
ማንም የለም ያፈረ አንተን ተማምኖ
ማንም የለም የወደቀ አንተን ጠብቆ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ