Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተን ተጠማች

Anten Tetemach

ትራክ 8 · 5:07 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ነፍሴም እንደ ውኃ አንተን ተጠማች

በቀንም በማታም እየናፈቀች (፪x)

ያሰብኩት ተሳክቶ እርካታ ሳይኖረኝ

ኢየሱስ ግን ሲመጣ ህይወት ፈለቀልኝ (፪x)

እኔማ አላይ ወደሌላ

የልቤ ሚገባው ሌላ የለምና

ኑሮዬም ቢሞላ ሚመች

እርካታዬ ኢየሱስ ስለሆነ እንጂ

ደመና አልባ ሰማይ ተንጣሎ ከፊቴ

ወጀብ ሲያፏጭባት ተፋልሳ ሕይወቴ

በማይቋጭ ዙሪት ተስፋ አጥቼ ሳለሁ

የዘላለም ተስፋ ኢየሱስን አገኘው (፪x)

እኔማ አላይ ወደሌላ

እርካታ ሚሞላ ሌላ የለምና

ኑሮዬም ቢሞላ ሚመች

እርካታዬ ኢየሱስ ስለሆነ እንጂ

በልቶም ይርበዋል አግኘቶ ይጐለዋል

ዛሬ አገኘሁኝ ሲል ኪሳራ ይቀድመዋል

ከምንጩ የሸሸ ነፍስ ከአንተ ርቆ የሄደ

የወጣ ሲመስለው ወደታች ወረደ (፪x)

እኔማ አላይ ወደሌላ

እርካታ ሚሞላ ሌላ የለምና

ኑሮዬም ቢሞላ ሚመች

እርካታዬ ኢየሱስ ስለሆነ እንጂ

እርካታዬ ኢየሱስ ነው

እርካታዬ (፰x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ