ማን እንዳንተ
Man Endante
2012 · ትራክ 8 · 5:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ልከፍለው የማልችል ነበረብኝ ዕዳ
ችግሬን ባዋየው ማን እኔን ሊረዳ
ኃጥያተኛ ብሎኝ ሁሉም ተጸየፈኝ
እንዲፈረድብኝ ጠላትም ከሰሰኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ማነው የሚያድነኝ ከእንግዲህ ብዬ
ብቻዬን ሳለቅስ አገኘኝ ጌታዬ
ዕዳዬን ተወልኝ እንባዬን አበሰው
የሕይወቴን ቁስል በቁስሉ ፈወሰው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙ ኃጥያቴ ተሰርዮልኛል
አብዝቼ እንድወደው በእርግጥ ይገባኛል
ዋጋው የከበረ የሽቶ መስዋዕት
ከደስታ እንባ ጋር ምነው ባቀርብለት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ለቅሶዬን ለደስታ እርሱ ከለወጠው
ሽቶ ላፈስለት ብልቃጡን ብሰብረው
ማነው ቅር የሚሰኝ ጌታዬን ባከብረው
ሃብቴን ብቻ ሳይሆን ሕይወቴን ብሰጠው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ማንም በውድቀቴ ያላዘነልኝን
በምድር ላይ ፍፁም ተስፋ የሌለኝ
ሞቴን ወደ ሕይወት መለሰው ኢየሱስ
ስለፍቅርህ ብዛት ሥምህን ልቀድስ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ማን እንዳንተ ጌታ ልብን ሊመረምር
ማን ጠልቆ ሊረዳ የሰዎችን ችግር
ዕውቀትህ የላቀ መሃሪዬ ነህ
ምሥጋናና ክብር ይሁን ለሥምህ
ይሁን ለሥምህ (፪x)
ይሁን ለሥምህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ