አዎን ይሆናል
Awon Yehonal
2012 · ትራክ 13 · 6:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በጌተ ሰማኒ ጌታ ኢየሱስ ቃቶ
በቀራንዮ ላይ ከጠላት ተዋግቶ
በጐቹን አድኗል ነፍሱን ለሞት ሰጥቶ
እንዲህ ያለ ፍቅር ከየት ይገኛል ከቶ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መልካም እረኛ ስለ በጐቹ
ነፍሱን ያኖራል በእርሱ የሚገባ
በእርሱም የሚሰማራ ለዘለዓለም ይድናል
ዘለዓለም ይኖራል
መንጋውን ሊበትን እረኛውን መቶ
ሰይጣን ቢጣጣርም እጅግ ተበራቶ
ምርኮውንም መልሷል ኢየሱስ ድል ነስቶ
ዛሬም ይደግመዋል ሕዝቦቹን ጐብኝቶ (፫x)
አዝማች · Chorus
አዎን ይሆናል መቼ ይቀራል
ቁጥር 3 · Verse 3
እንጠብቃለን ለቅሷችንን በደስታ
ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሃዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል
ዓለም የሌላትን መድህን አግኝተናል
ስለዚህም እኛ ምንም ብንገፋ
ማንም አይጥለንም ከዚህ ፅኑ ተስፋ (፫x)
አዝማች · Chorus
አዎን ይሆናል መቼ ይቀራል
ቁጥር 5 · Verse 5
እንጠብቃለን ለቅሷችንን በደስታ
ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
በቅርብ በሩቅ የተበተናችሁ
ጌታ ቅርብ ነውና ፍፁም አይክፋችሁ
የእርሱን በጐነት ለዓለም ተናግራችሁ
ለጽዮን ስብሰባ በእግዚአብሔር ያብቃችሁ (፫x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ቶሎ ና
ናና ሰብስበን ከተበታተንበት
ወደ ውድ አገራችን ጥራን አከማቸን (፪x)
አዝማች · Chorus
አዎን ይሆናል መቼ ይቀራል
ቁጥር 8 · Verse 8
እንጠብቃለም ለቅሷችንን በደስታ
ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን (፪x)
ቁጥር 9 · Verse 9
አዎን ይሆናል (አዎን ይሆናል)
መቼ ይቀራል (መቼ ይቀራል)
እንጠብቃለን ለቅሷችንን በደስታ
ኢየሱስ ለውጦልን ብርሃንን እናያለን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ