Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክብር ለኢየሱስ ይሁን

Keber Leyesus Yehun

2012 · ትራክ 7 · 4:45 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በቀራንዮ መስቀል ላይ በደዌ የደቀቀው

ነፍሱን ስለ ኃጥያቴ መስዋዕት ያደረገው

የሞትን ቀንበር ሰብሮ እኔኑ ሊያወጣ ነው

ማዳኑን ቀምሻለው ምን አለ የምመልሰው (፪x)

ክብር ለኢየሱስ ይሁን

አየን አሸናፊነቱን

ኃያል እንደ እርሱ የለም

ይንገሥ ለዘለዓለም (፪x)

የተናቀ ደካማ ቢመስልም አመጣጡ

ከእሰይ ልጅ ከዳዊት ሥር የወጣው ቁጥቋጡ

ኢየሱስ አሸነፈ ፍሬው ምድርን ሸፈነ

የእግዚአብሔር ፈቃድ በእጁ ተከናወነ (፪x)

ክብር ለኢየሱስ ይሁን

አየን አሸናፊነቱን

ኃያል እንደ እርሱ የለም

ይንገሥ ለዘለዓለም (፪x)

በደሙ ኃይል ጸደቅን በሥሙ ድል አገኘን

ማነው የሚቋቋመን ማንስ ነው የሚገታን

እንገሰግሳለን አሸናፊውን ይዘን

ወደ ቅድስቷ ሃገር በድል እንገባለን (፪x)

ክብር ለኢየሱስ ይሁን

አየን አሸናፊነቱን

ኃያል እንደ እርሱ የለም

ይንገሥ ለዘለዓለም (፪x)

ክብር ምሥጋና ይዘን ከፊቱ እንቀርባለን

በዙፋኑ ላይ ላለ እንሰግድለታለን

ሁሉን የረታ ጌታ ንገሥ እንለዋለን

አቤት ለዘለዓለም እርሱ ኃያል ነው አሜን (፪x)

ክብር ለኢየሱስ ይሁን

አየን አሸናፊነቱን

ኃያል እንደ እርሱ የለም

ይንገሥ ለዘለዓለም (፭x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ