በወንጌል እውነት
Bewengiel Ewnet
2012 · ትራክ 10 · 5:02 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በወንጌል እውነት ወገቡን ታጥቆ
ስለ ሕይወት ቃል ጸንቶ ተዋድቆ
በጌታ ብርታት የከበበውን ጭፍራ ሰንጥቆ
በጐ ወታደር በድል አለፈ ያንን የሞትን ሸለቆ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለተጨነቀ ልቡ እረፍት አግኝቶ
ጉዞውን ቢጀምር ወደ ሰማያዊ አገር አቅንቶ
ሰይጣን በተንኮል በወጥመዱ አጥሮ መንገድ ቢዘጋበት
ጌታም ይህን አይቶ ወጥመዱን ሰባብሮ በሩን ከፈተለት
አዝማች · Chorus
በወንጌል እውነት ወገቡን ታጥቆ
ስለ ሕይወት ቃል ጸንቶ ተዋድቆ
በጌታ ብርታት የከበበውን ጭፍራ ሰንጥቆ
በጐ ወታደር በድል አለፈ ያንን የሞትን ሸለቆ
ቁጥር 2 · Verse 2
መዋጋትን እንዲለምድ ሸለቆ ወርዶ
ከቤት ከንብረቱ ከነፍሱ አብልጦ ጌታውን ወዶ
ሰልፉ በረታና ክፉኛ ተጠቅቶ እጅና እግሩ ዝሎ
ኢየሱስ ደርሶለት ድልን አወጀለት ባላንጣውን ጥሎ
አዝማች · Chorus
በወንጌል እውነት ወገቡን ታጥቆ
ስለ ሕይወት ቃል ጸንቶ ተዋድቆ
በጌታ ብርታት የከበበውን ጭፍራ ሰንጥቆ
በጐ ወታደር በድል አለፈ ያንን የሞትን ሸለቆ
ቁጥር 3 · Verse 3
እጆቹን በእርፉ ላይ አንዴ አሳርፏል
ወደኋላ ማየት ነውር በመሆኑ ሥራውን ቀጥሏል
እምነት ሳይጓደል አደራ ሳይበላሽ ተጠንቅቆ ታግሎ
እፎይ ማለቱ ነው በክብር ተራራ አክሊል ተቀብሎ
አዝማች · Chorus
በወንጌል እውነት ወገቡን ታጥቆ
ስለ ሕይወት ቃል ጸንቶ ተዋድቆ
በጌታ ብርታት የከበበውን ጭፍራ ሰንጥቆ
በጐ ወታደር በድል አለፈ ያንን የሞትን ሸለቆ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ