ሁሉን የምትገዛ
Hulun Yemetgeza
2012 · ትራክ 3 · 5:24 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የጽድቅ ሥራህን ጌታ ሰራህና
በጨለማ ላሉ ፀሐይ ወጣችና
ከዘለዓለም ጥፋት አንተ ያዳንካቸው
በታዳጊነትህ እጅግ ደስ አላቸው (፪x)
አዝማች · Chorus
ሁሉን የምትገዛ ያለህ የነበርህ
ትልቁን ኃይልህን ለብሰህ የከበርህ
ሥምህ ለዘለዓለም ይመስገን ይባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ጌታ ሆይ ይንበርከክ
ቁጥር 2 · Verse 2
የመስቀል ፍቅርህን ለሰው ይነግራሉ
የቅድስናህን ክብር ያወራሉ
በክንፎችህ ጥላ ታምነው ይኖራሉ
የማዳን ክንድህን ሁልጊዜ ያያሉ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሁሉን የምትገዛ ያለህ የነበርህ
ትልቁን ኃይልህን ለብሰህ የከበርህ
ሥምህ ለዘለዓለም ይመስገን ይባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ጌታ ሆይ ይንበርከክ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከሥም ሁሉ በላይ ሥምህ የከበረ
ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ ያማረ
የሚመስልህ የለም እጅግ ልዩ ነህ
ከፍ ብለህ ንገሥ ግርማ ተሞልተህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሁሉን የምትገዛ ያለህ የነበርህ
ትልቁን ኃይልህን ለብሰህ የከበርህ
ሥምህ ለዘለዓለም ይመስገን ይባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ጌታ ሆይ ይንበርከክ
ቁጥር 4 · Verse 4
ክብርህ በምድር ሁሉ ይታይ አምላካችን
ምላስም ይመስክር ታላቅነትህን
በሰማይ በምድር ትሰለጥናለህ
ሁሉም ከእግርህ በታች አንተ ትገዛለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሁሉን የምትገዛ ያለህ የነበርህ
ትልቁን ኃይልህን ለብሰህ የከበርህ
ሥምህ ለዘለዓለም ይመስገን ይባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ጌታ ሆይ ይንበርከክ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ