መድኃኒታችን
Medhanitachen
2012 · ትራክ 6 · 6:24 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር አምላክ እኛን በመውደዱ
በዘለዓለም ምክሩ በበጐ ፈቃዱ
ውድ ልጁን ልኮ ከኃጥያት አዳነን
ገንዘቡም ሊያደርገን ዋጋ ከፍሎ ዋጀን
መድኃኒታችን ከአመፅ ተቤዠን
በደሙ አንጽቶ ለእራሱ ቀደሰን
የመንግሥቱም ወራሽ ወገን አደረገን
የናዝሬቱ ኢየሱስ በፀጋ ተሞልቶ
የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ተቀብቶ
ሕዝቡን እየፈታ ዞረ እየፈወሰ
የዲያቢሎስንም ሥራ እያፈረሰ
የአምላካችን ማዳን የታዳጊነቱ
ዝናውም ሲነገር የኃያልነቱ
ጠላት ተቀጥፈዋል ነደደ:መኣቱ
ሊቀ ካህናቱ የአይሁድም አለቆች
ሄሮድስ ጲላጦስ የዛ ዘመን ዳኞች
ቢመረምሩትም በደል አጡበት
ጻድቅ ነው ጌታችን የለውም ስህተት
ነውርና እድፍ ነቀፋ የሌለው
መስዋዕት በመሆን ስለ እኛ የሞተው
ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ጀርባውን በጅራፍ በእጅጉ ገርፈው
እጆቹን እግሮቹን በምስማር ቸንክረው
በመስቀል አዋሉት እንደ በደለኛ
የነፍሳቸውን ዋስ ያን ታማኝ እረኛ
የሚያደርጉትን ባለማወቃቸው
አብ ኃጥያታቸውን እንዳይዝባቸው
እርሱ ግን ማለደ ይቅር እንዲላቸው
መተላለፋችን ተግሳጽ ውጣታችን
ደዌ ህመማችን ስቃይ መከራችን
በምህረቱ አዋጅ ወደቀ ከእዳችን
በኢየሱስ ቤዛነት ተሻረ ሞታችን
አዝማች · Chorus
በእርሱ ስላገኘን ሰላምና እርካታ
ሃዘንን በደስታ ዋይታን በዕልልታ
ስለ ለወጠልን ይክበር የእኛ ጌታ
በአንተ ስላገኘን ሰላምና እርካታ
ሃዘንን በደስታ ዋይታን በዕልልታ
ስለ ለወጥክልን ይክበር የእኛ ጌታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ