Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምሥጋና

Mesgana

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በመገረፉ ቁስል ቁስሎቼን ፈውሶ

በፍቅር እጆቹ እምባዬን አብሶ

ይህን ከዚህ ዘመን በሰላም እዘረጋለሁ???

ለመረጠኝ አምላክ ምሥጋናን እሰዋለሁ

ምሥጋና (፫x) የጌታዬን ማዳን አይቻለሁና

ምሥጋና (፫x) የአምላኬን ማዳን አይቻለሁና

የገማ ቢኖርም አራት ቀን ያለፈው

የእኔ ጌታ ኢየሱስ የትንሳኤ አምላክ ነው

ለእኔ ሲከብድብኝ ወደ እርሱ እሮጣለሁ

መቅረዙ ተፈቶ ሕያው ሆኖ አያለሁ

ምሥጋና (፫x) የጌታዬን ማዳን አይቻለሁና

ምሥጋና (፫x) የአምላኬን ማዳን አይቻለሁና

የቁጣ ግልምጫ የክፋት እርግጫ

ቢፈራረቅ እንኳን የግፈኞች ቁጫ???

ከላይ የሚያይ ጌታ በጥማት ስንጫጫ

የማዕዘኑ አለት ሆኖኛል ማምለጫ

ምሥጋና (፫x) የጌታዬን ማዳን አይቻለሁና

ምሥጋና (፫x) የአምላኬን ማዳን አይቻለሁና

ቀኖች ክፋታቸው እጥፍ ቢጨምሩ

የማመልከው አምላክ ይበልጣል ከሁሉ

ይሄ ብልጭልጩ ሁሉ ነገር ሲያልቅ

ውዴ ከተፍ ይላል ልጆቹን ሊያሳርፍ

ምሥጋና (፫x) የጌታዬን ማዳን አይቻለሁና

ምሥጋና (፫x) የጌታዬን ማዳን አይቻለሁና

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ