ሲንከባለል
Sinkebalel
ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በረጅም ዘመን የፈሰሰ እምባ
ወደ ላይ ሰንጥቆ አርያም ሲገባ
ጌታም ዘንበል ሲል ይታየኛል እኔ
የተናገረውን ሲፈፅም በዐይኔ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሲንከባለል ድንጋዩ
ጠልን ሲሰጥ ሰማዩ
የምድር ፍሬ ሲለምልም
ጻድቅ በምሥጋና ይግነን (፪x)
አዝማች · Chorus
በረጅም ዘመን የፈሰሰ እምባ
ወደ ላይ ሰንጥቆ አርያም ሲገባ
ጌታም ዘንበል ሲል ይታየኛል እኔ
የተናገረውን ሲፈፅም በዐይኔ
ቁጥር 2 · Verse 2
ምናምንቴው ተራግፎ
የከበረው ተሰልፎ
ጌታን ያየ በክብር
እንዲህ ይበል ከእኔ ጋር (፪x)
አዝማች · Chorus
በረጅም ዘመን የፈሰሰ እምባ
ወደ ላይ ሰንጥቆ አርያም ሲገባ
ጌታም ዘንበል ሲል ይታየኛል እኔ
የተናገረውን ሲፈፅም በዐይኔ
ቁጥር 3 · Verse 3
ይሽሩን ሆይ ብሎታል
በቁልምጫ ጠርቶታል
በደመናት እንደሚሄድ
እንደ እግዚአብሔር ያለ የለም (፪x)
አዝማች · Chorus
በረጅም ዘመን የፈሰሰ እምባ
ወደ ላይ ሰንጥቆ አርያም ሲገባ
ጌታም ዘንበል ሲል ይታየኛል እኔ
የተናገረውን ሲፈፅም በዐይኔ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሲቆረቆር ምሥጋና
ተኖ ሲሄድ በደመና
ያሸተዋል መስዋዕቴን
እኔም ላብዛ ምሥጋናዬን (፪x)
አዝማች · Chorus
በረጅም ዘመን የፈሰሰ እምባ
ወደ ላይ ሰንጥቆ አርያም ሲገባ
ጌታም ዘንበል ሲል ይታየኛል እኔ
የተናገረውን ሲፈፅም በዐይኔ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ