ጌታ አበረታኝ
Geita Aberetagn
ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ
ኢየሱስ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ
ፈጥኖ ደረሰና ከክፉ ፊት ቀድሞ
ነፍሴን ከሚዋጋ ከክፉ ፊት ቀድሞ
ቁጥር 1 · Verse 1
አሰላስላለሁ የጌታን በጐነት
በእኔ ላይ ያለውን የአላማውን ፅናት
ጌታ አስደንቆኛል አመስግን ይለኛል
ምህረቱን ልዘምር በእርግጥ ይገባኛል
ማዳኑን ልናገር በእርግጥ ይገባኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ
ኢየሱስ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ
ፈጥኖ ደረሰና ከክፉ ፊት ቀድሞ
ነፍሴን ከሚዋጋ ከክፉ ፊት ቀድሞ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሲጣሉ ብቻቸው ሲታዩ ግን በዙ
ከእሳት የሚታደግ ማን ይሆን ጐበዙ
የነገሥታት ንጉሥ የኃያላን ሃያል
በምስሉ ላይሰግዱ ከሚጨክኑት ጋር
ይቆማል እግዚአብሔር ስሙን ሊያስከብር
ጌታ አስደንቆኛል አመስግን ይለኛል
ምህረቱን ልዘምር በእርግጥ ይገባኛል
ማዳኑን ላወራ በእርግጥ ይገባኛል
አዝማች · Chorus
ጌታ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ
ኢየሱስ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ
ፈጥኖ ደረሰና ከክፉ ፊት ቀድሞ
ነፍሴን ከሚዋጋ ከክፉ ፊት ቀድሞ
ቁጥር 3 · Verse 3
በአርጤክስስ ዘመን የሞት አዋጅ ወጣ
አይሁድ እንዲወገድ ዝክሩ እንዲታጣ
አዋጁን ለወጠው ሞትን ገለበጠው
ከላይ ተፈርዶበት ጽዋውን ጨለጠው
እግዚአብሔር ተዋጊ ስሙም እግዚአብሔር ነው
ጌታ አስደንቆኛል አመስግን ይለኛል
ምህረቱን ልዘምር በእርግጥ ይገባኛል
ማዳኑን ልናገር በእርግጥ ይገባኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ
ኢየሱስ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ
ፈጥኖ ደረሰና ከክፉ ፊት ቀድሞ
ነፍሴን ከሚዋጋ ከክፉ ፊት ቀድሞ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ