ይቻላል
Yechalal
ትራክ 6 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ይቻላል አዎን ይቻላል
ይቻላል በእርግጥ ይቻላል
በእግዚአብሔር ዐይን እጅግ ቀላል ነው
እኛ ያቃተን ለእርሱ ምኑ ነው (፪x)
ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል
በጌታ ሁሉ ይቻላል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰላሳ ስልሳ መቶ የክፉን ሃይል አጥፍቶ
ለአምላክ ይቻላል ለአባት ይቻላል
ከልካዩን ልከለክል አዳኙን ልናድነው
ስሙ ሃያል ነው ስሙ ሃያል ነው
ችሎ የሚያስችለኝ ጌታ እያለኝ
ለምን ስንፍናን አወራለሁኝ
አዝማች · Chorus
ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል
በጌታ ሁሉ ይቻላል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የቀደሙት አባቶች የእምነት ምሳሌዎች
የፅድቅ አርበኞች ቆራጥ ጨካኞች
መንግሥታትን ድል ነሱ ጭፍሮችን አባረሩ
ድልን ዘመሩ በድል ዘመሩ
ቁጥር 3 · Verse 3
በአምላኬ ሁሉ ይቻላል
ቁጥር 4 · Verse 4
በጌታ ሁሉ ይቻላል (፪x)
ይቻላል አዎን ይቻላል
ይቻላል በእርግጥ ይቻላል
በእግዚአብሔር ዐይን እጅግ ቀላል ነው
እኛ ያቃተን ለእርሱ ምኑ ነው (፪x)
የእሳትን ሃይል አለፉ ክፉውን ጥሰው አለፉ
በእምነት ድል ነሱ (፪x)
የአናብስትን አፍ ዘጉ በእምነት እያደጉ
ሄዱ ተጠጉ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይቻላል አዎን ይቻላል
ይቻላል በእርግጥ ይቻላል
በእግዚአብሔር ዐይን እጅግ ቀላል ነው
እኛ ያቃተን ለእርሱ ምኑ ነው (፪x)
ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል
በጌታ ሁሉ ይቻላል (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ሃይልን በሚያስታጥቀን በአምላካችን ታምነን
እንገባለን እንወጣለን
ቃሉም እንደሚነግረን በእርሱ ከአሸናፊዎች
እንበልጣለን እንበልጣለን
ችሎ የሚያስችለኝ ጌታ እያለኝ
ለምን ስንፍናን አወራለሁኝ
አዝማች · Chorus
ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል
በጌታ ሁሉ ይቻላል (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
እንወራረዳለን ለምስሉ አንሰግድም
ጌታ ይረዳናል (፪x)
እውነትን እንሸሽግም በወንጌል ደግሞ አናፍርም
ኢየሱስ ያድናል (፪x)
አዝማች · Chorus
ይቻላል አዎን ይቻላል
ይቻላል በእርግጥ ይቻላል
በእግዚአብሔር ዐይን እጅግ ቀላል ነው
እኛ ያቃተን ለእርሱ ምኑ ነው (፪x)
ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል
በጌታ ሁሉ ይቻላል (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ