ተንቀን አንቀርም
Teneqen Anqerem
ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ደስታችን በምድር ፍፁም ባይሆን እንኳን
ልባችን ሲመታ በመከራ ሃዘን
የጌታን መገለጥ በመጠበቃችን
የምንጽናናበት አዲስ አገር አለን
አዝማች · Chorus
ተንቀን አንቀርም ተጥለን በምድር
አዲስ አገር አለን ከአድማስ ባሻገር
ጌታም ይመለሳል ዳግም ሊያሳርፈን
ቁጥር 2 · Verse 2
በገዛ ዙፋኑ በቀኝ ሊያስቀምጠን
የምድር መጽዐተኛ ባለ ፅኑ ተስፋ
በላይ ያለው ሽቶ በምድር የተገፋ
ባይደላውም እንኳን ፀንቶ በመታገስ
በክብር ያየዋል የናፈቀውን ንጉሥ
አዝማች · Chorus
ተንቀን አንቀርም ተጥለን በምድር
አዲስ አገር አለን ከአድማስ ባሻገር
ጌታም ይመለሳል ዳግም ሊያሳርፈን
ቁጥር 3 · Verse 3
በማያልፈው መንግሥት ዘለዓለም ሊያነግሰን
የዚህን ዓለም ሃሳብ ታግሎ ያሸነፈ
በመከራ ፀንቶ በትዕግሥት ያለፈ
አምላኩ ሲገለጥ እጅጉን ይፅናናል
ያልተሰማ ዜማን ውዳሴን ያፈልቃል
አዝማች · Chorus
ተንቀን አንቀርም ተጥለን በምድር
አዲስ አገር አለን ከአድማስ ባሻገር
ጌታም ይመለሳል ዳግም ሊያሳርፈን
ቁጥር 4 · Verse 4
በማያልፈው መንግሥት ዘለዓለም ሊያነግሰን
መከራም ይረሳል ሃዘንም ይቀራል
ያናዝሬቱ ኢየሱስ እምባችንን ያብሳል
ጻድቅ ፈራጃችን በቅርብ ይገለጣል
የወጉትም ዐይኖች ፊት ለፊት ያዩታል
አዝማች · Chorus
ተንቀን አንቀርም ተጥለን በምድር
አዲስ አገር አለን ከአድማስ ባሻገር
ጌታም ይመለሳል ዳግም ሊያሳርፈን
ቁጥር 5 · Verse 5
በገዛ ዙፋኑ በቀኝ ሊያስቀምጠን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ