ነፍሴን ያዳነው
Nefsien Yadanew
ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በዘሬ አይግባ ያልኩት
ከመንደሬ ገፍቼ ያወጣሁት
እርሱ ነው ነፍሴን ያዳንው
በሞት መሃል የደረሰው
ቀንበሬን የሰበረልኝ
ኢየሱስ ይባረክልኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
በጎነቱ ሲነገረኝ ማዳኑ መቼ ማረከኝ
ጆሮዬን በእጄ ዘግቼ ኢየሱስን አይን ላፈር አልኩኝ
መራቡን ያላወቀ ሰው እንዴት እንጀራ አንስቶ ይብላ
ኋላ ግን ሲሞረሙረው ይሻዋል ቀድሞ እንዳልበላ
አዝማች · Chorus
በዘሬ አይግባ ያልኩት
ከመንደሬ ገፍቼ ያወጣሁት
እርሱ ነው ነፍሴን ያዳንው
በሞት መሃል የደረሰው
ቀንበሬን የሰበረልኝ
ኢየሱስ ይባረክልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
መስቀሉን በጀርባው ጭኜ
ጦሬን መዝዤ ጨክኜ
ጎልጎታ ድረስ ወሰድኩት
እጁን ቸንክሬ ሰቀልኩት
ከአዘነለት ሰው ይልቅ ምህረቱ ለኔ ቀደመ
ሚያደርገውን አያውቅምና አባት ሆይ ማረው ተባለ
አዝማች · Chorus
በዘሬ አይግባ ያልኩት
ከመንደሬ ገፍቼ ያወጣሁት
እርሱ ነው ነፍሴን ያዳንው
በሞት መሃል የደረሰው
ቀንበሬን የሰበረልኝ
ኢየሱስ ይባረክልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኃጢያቴ በዝቶ በደጄ ሊገድለኝ ሲጥር ሲያደባ
ባፈሰስኩበት ደሙ አጥቦ ሊያነፃኝ ቃል ገባ
አጥንቴ ደቆ ስቆዝም አይዞህ የሚል ሰው ሲጠፋ
ኢየሱስ ግን ለእኔ ደረሰ ያኔ በእጄ የተገፋ
አዝማች · Chorus
በዘሬ አይግባ ያልኩት
ከመንደሬ ገፍቼ ያወጣሁት
እርሱ ነው ነፍሴን ያዳንው
በሞት መሃል የደረሰው
ቀንበሬን የሰበረልኝ
ኢየሱስ ይባረክልኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
አጥላልቼው ከወደደ ለሰቀልኩት ከማለደ
ምን ይሆንለት ምላሹ እንደ ስራዬ ካላዋረደኝ
ኢየሱሴ አድነኝ ስለው ያኔ ምን አረክ አላለም
እንደ እርሱ ትሁት ቸር የለም ስሙ ይባረክ ዘላለም
አዝማች · Chorus
በዘሬ አይግባ ያልኩት
ከመንደሬ ገፍቼ ያወጣሁት
እርሱ ነው ነፍሴን ያዳንው
በሞት መሃል የደረሰው
ቀንበሬን የሰበረልኝ
ኢየሱስ ይባረክልኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
ኃጢያቴን ያልቆጠረብኝ
ምህረቱን ያበዛልኝ
ቸርነቱን ያወረደው ኢየሱስ ይባረክልኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ