ክብርን እንሰጣለን
Keberen Ensetalen
ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ልባችንን ከእጃችን ጋር
በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር
እናነሳለን ክብርንም እንሰጣለን
እናመልካለን በፊቱ እንሰግዳለን
ሰማይ ዝፋንህ ነው መቀመጫህ
ምድርም ለእግሮችህ መርገጫህ
ለትልቅነትህ ወሰን ነህ የሌለህ
ሰማያትንም በስንዝር የለካህ
ቁጥር 2 · Verse 2
እንሰግዳለን ለአንተ ክብር ይሁን ጌታ
ልባችንን ከእጃችን ጋር
በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር
እናነሳለን ክብርንም እንሰጣለን
እናመልካለን በፊቱ እንሰግዳለን
ቁጥር 3 · Verse 3
እስትንፋሽን ለሙታን ትሠጣለህ
በባዶ ሸለቆ ውሃን ትሞላለህ
ጥበብህን ችሎታህን ማን ይለካዋል
ያልነበርን እንደምታኖር አውቀዋል
ከፍ ያልከው ጌታ ክብር ይገባሃል
አዝማች · Chorus
ልባችንን ከእጃችን ጋር
በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር
እናነሳለን ክብርንም እንሰጣለን
እናመልካለን በፊቱ እንሰግዳለን
ቁጥር 4 · Verse 4
እንዲበላ እንዲጠጣ ለራሱ እንዲኖር
ብቻ አልነበርም ሰውን በእጅህ መስራት
እንዲያመልክህ በታላቅነት እንዲያከብርህ
መሆኑን ተረድቻለሁ እኔን መፍጠርህ
ታላቅ ነህ አንተ ጌታ ሆይ ክብር ይሁንልህ
አዝማች · Chorus
ልባችንን ከእጃችን ጋር
በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር
እናነሳለን ክብርንም እንሰጣለን
እናመልካለን በፊቱ እንሰግዳለን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ