የንጋት ኮከብ
Yenegat Kokeb
ትራክ 9 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ
ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ
የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ
ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ
ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ
ቁጥር 1 · Verse 1
የነገስታትን ኩራት ባዶ ያረገ
ለምስኪኖች መንገሻ መንገድ ጠረገ
የዚህችን አለም ጥበብ ለማሳፈር
እኛን ሞኞች መረጠ ዘላለም ይክበር
አዝማች · Chorus
የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ
ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ
የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ
ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ
ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ
ቁጥር 2 · Verse 2
ደረቱን በወርቅ መታጠቂያ ታጠቀ
ጉስቁልናን ከልጆቹ አራቀ
አኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው
ጨለማን ያስወገደ ክብሩን ታላቅ ነው
አዝማች · Chorus
የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ
ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ
የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ
ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ
ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከሰማይ በአመጻው የተወለደ
በምድርም በሰዎች ላይ ሞት ያወረደ
ኢየሱስ ከላይ ሲገለጥ የእኛ አባባ
ጠላት የለም የታለ የት እንደ ገባ
አዝማች · Chorus
የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ
ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ
የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ
ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ
ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ
ቁጥር 4 · Verse 4
በአራቱም ማዕዘናት ክብሩ እያበራ
ውዳችን ይገለጣል ከመላዕክት ጋራ
ከእርሱ ጋር ስንሻገር ከአድማስ ወዲያ
ተስፋችን ይፈጸማል ኦ ሃሌሉያ
አዝማች · Chorus
የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ
ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ
የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ
ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ
ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ