ኃይልህ ብዙ ሲሆን
Hayleh Bezu Sihon
ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ
የቁጣቸው ግለት በላይህ በረደብህ
ምን ልበል ታዲያ ውዴ ምንስ ልክፈልህ
በአንተ አረፈች ነፍሴ ለዘላለም ታመስግንህ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያ አስፈሪው ግርማህ ለአንዳፍታ ተቀይሮ
ጌታነትህ ክብር በባርነት ተመንዝሮ
የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ አራስህን አድን ሲሉህ
የእኔን ቂም በእንተ በመስቀል ሲወጡ
ነፍሴ ወጣች ከእስራቱ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ
የቁጣቸው ግለት በላይህ በረደብህ
ምን ልበል ታዲያ ውዴ ምንስ ልክፈልህ
በአንተ አረፈች ነፍሴ ለዘላለም ታመስግንህ
ቁጥር 2 · Verse 2
የሰው አንቆቅልሽ በአንተ ዘንድ ምላሽ ሲያገኝ
ለተገፊዎቹም ችሎት ቀርበህ ስትል ይግባኝ
በአንተ መገፋት ግን ሰማይ ምድር ዝም ሲሉ
ሃይልህ አስኪገለጥ አጅግ ቢያቃልሉህ
በክንድህ ሲዖል ተጣሉ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ
የቁጣቸው ግለት በላይህ በረደብህ
ምን ልበል ታዲያ ውዴ ምንስ ልክፈልህ
በአንተ አረፈች ነፍሴ ለዘላለም ታመስግንህ
ቁጥር 3 · Verse 3
የክፋቴ ብዛት በሰው አፍ መርገም ሆኖ
ወሬ ለሚሰማ ለሚያይም አይን አስጨፍኖ
በሰፈሬ ስታልፍ ያንን ስድቤን ስትሸከም
በቁጣው ስትደርቅ ነፍሴን ለማለምለም
ከፍ በል ለዘለዓለም
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ
የቁጣቸው ግለት በላይህ በረደብህ
ምን ልበል ታዲያ ውዴ ምንስ ልክፈልህ
በአንተ አረፈች ነፍሴ ለዘላለም ታመስግንህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ቆሞ በምድር ላይ ከህያዋን መቀላቀል
በሚመጣውም አለም ብቤትህ አኔን ስትቀበል
ከዚያም አልፎ የጓዳዬ መከራ ሲረሳ
ከአንተ የተነሳ ቀረ ያ አበሳ
ክበር የይሁዳ አንበሳ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ
የቁጣቸው ግለት በላይህ በረደብህ
ምን ልበል ታዲያ ውዴ ምንስ ልክፈልህ
በአንተ አረፈች ነፍሴ ለዘላለም ታመስግንህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ