የሚጤስ ጧፌን አላጠፋም
Yemitesewen Tuafien Alatefam
ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሚጤስ ጧፌን አላጠፋህም
ቅጥቅጥ ሸምበቆዬን ከቶ አልሰበርክም
ምሕረትህ በእኔ እጀጉን በዝቷል
የማዳን ክንድህን ዓይኔ አይቶታል
ቁጥር 2 · Verse 2
ክበር ተመስገን (፫) ዘላለም
እንዳንተ ያለ የለም(፪)
(፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
1)ቅጥቅጥ ሸንበቆን ጌታ የት ተሰብራለህ
የሚጠሰውንስም ጧፍ መች ታጠፋለህ
በሕይወት ታኖራለህ እንጂ ከቶ አትሰብርም
ይህ ነው ሥራህ ጌታ ክበር ለዘለዓለም
እጅግ በደሌ በዝቶ የተዋረድኩ
ዓይኔ ባንተ ተከፍቶ ጽድቅን አየሁ
ሕይወትን ይዘህ ጌታ መጣህ ወደኔ
ለነፍሴ ቤዛ ሆንክ ክበር መድሃኔ
አዝማች · Chorus
2)እስከ ቀራንዮ ድረስ ጉድ ተሸክመህ
ነብሴ በነብስህ ሲዋጅ ታሪክ ተፈፀመ
የመዳኔ ምልክት ያኔ ታተመ
የሰበረኝ ሀጥያቴ ጉልበቱ አከተመ
ፍቅርህ እስከሞት ለኔ የበረታ ነው
ከጥፋት ጉድጓድ ደርሶ ነብሴን አዳነው
በኔ መቃብር ገብተህ ህይወት ሆነሀል
የሚጤሰውን ጧፌን ጌታ አብርተሀል
3)38 አመት እግሬን አጥቼ
በቤተ ሳይዳ ደጃፍ በዋዛ ተኝቼ
ሰው እንደማይቀርበኝም ባይንህ አየኸኝ
እጆቼን ይዘህ ጌታ በእግሬ አቆምከኝ
እንኳን አልጋ ልሸከም መሄድ የማልችል
ፍፁም የተሳሰርኩኝ ሽባ ነበርኩኝ
ታምራትህን በህይወቴ አሳየኸኝ
ሌላ ምን እላለሁኝ ክበር ተመስገን
4)ወደ ባሪያህ ሕዝቂያስ ዓይንህን መልሰህ
በዕድሜው ላይ 15 ዓመት ጨምረህ
የፈሰሰውን ዕንባ ከዓይኖቹ አበስከው
በሕይወት እንዲኖር የሱስ ፈወስከው
የሕዝቅያስስ ታሪክ የሕዝቅያስ ነው
ለኔ ያደረክልኝ እጅግ ድንቅ ነው
በነፍስም በስጋዬም ሙት የነበርኩኝ
በቀራኒዮ ፍቅርህ በሕይወት ኑር አልከኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ