ቤትህ በተሰራ ጊዜ
Bieteh Betesera Gizie
ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቤትህ በተሰራ ጊዜ የድንጋይ ጩኸት አልነበረም
መራጃው ከቶ አልተንኳኳም
በተሸለሙ ድንጋዮች የተሰራ
ማን ታወከ መች ሆነ ተራራ
ዛሬ ግን ያለመረዳት እሩጫ ሆነ
በሰባራ ገል ቤትህ ተሰራ ተከናወነ
ኡ እኔስ ፈራሁ ጩኸቱ ሲበዛ
አውቄህ ልኑር ሰብስበኝ በቃልህ ጣዛ
ኡ እኔስ ፈራሁ የኔ ጌታ
እራሴን ልየው ከጠዋት እስከማታ
ቁጥር 1 · Verse 1
ድንጋዩ እንዳይታይ በዝግባ ሲለበጥ
ዝግባው ባማረ ወርቅ ሲያጌጥ
መስራትም መሰራትም ያኔ ነበረ
ይታያልም ክብር ሲገለጥ
ድንጋይ በድንጋይ ላይ ይፈርሳ ተባለ
መች ቀረ ይኸው አሁን ሆነ
ወንድም ከወንድሙ ጋራ ሳይጣበቅ
በጩኸት ሞቀ ቤቱ ጋለ
አዝማች · Chorus
ቤትህ በተሰራ ጊዜ የድንጋይ ጩኸት አልነበረም
መራጃው ከቶ አልተንኳኳም
በተሸለሙ ድንጋዮች የተሰራ
ማን ታወከ መች ሆነ ተራራ
ዛሬ ግን ያለመረዳት እሩጫ ሆነ
በሰባራ ገል ቤትህ ተሰራ ተከናወነ
ኡ እኔስ ፈራሁ ጩኸቱ ሲበዛ
አውቄህ ልኑር ሰብስበኝ በቃልህ ጣዛ
ኡ እኔስ ፈራሁ የኔ ጌታ
እራሴን ልየው ከጠዋት እስከማታ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘሩ በመንገድ ዳር ወድቆ ሲለቀም
በጭንጫ ላይ ያለው ሲከስም
ግማሹ በእሾህ መሃል ሲታነቅ
ባለ ፍሬ ጠፍቶ ሲደርቅ
ከወርቅ ይልቅ የሚፈተነው እምነት በዝማሬ ተመስሎ ጠፋ
ከነኣን ላይገባ በኢያሪኮ ዙሪያ ሞልቷል መለከት የሚነፋ
አዝማች · Chorus
ቤትህ በተሰራ ጊዜ የድንጋይ ጩኸት አልነበረም
መራጃው ከቶ አልተንኳኳም
በተሸለሙ ድንጋዮች የተሰራ
ማን ታወከ መች ሆነ ተራራ
ዛሬ ግን ያለመረዳት እሩጫ ሆነ
በሰባራ ገል ቤትህ ተሰራ ተከናወነ
ኡ እኔስ ፈራሁ ጩኸቱ ሲበዛ
አውቄህ ልኑር ሰብስበኝ በቃልህ ጣዛ
ኡ እኔስ ፈራሁ የኔ ጌታ
እራሴን ልየው ከጠዋት እስከማታ
ቁጥር 3 · Verse 3
እርስ በእርሳቸው የማይገላመጡ
ለእግዚአብሔር ክብር ሚሮጡ
አገልጋዮች የሉም ራሳቸውን የካዱ ማይነቀፉ የተለወጡ
ፍርድን ከራሱ ቤት ይጀምራልና
ወደ ህያው ድንጋይ እናቅና
በታቦት ብቻ እልልታን ከማቅለጥ
ኢየሱስን እንምሰል እንደግ
አዝማች · Chorus
ቤትህ በተሰራ ጊዜ የድንጋይ ጩኸት አልነበረም
መራጃው ከቶ አልተንኳኳም
በተሸለሙ ድንጋዮች የተሰራ
ማን ታወከ መች ሆነ ተራራ
ዛሬ ግን ያለመረዳት እሩጫ ሆነ
በሰባራ ገል ቤትህ ተሰራ ተከናወነ
ኡ እኔስ ፈራሁ ጩኸቱ ሲበዛ
አውቄህ ልኑር ሰብስበኝ በቃልህ ጣዛ
ኡ እኔስ ፈራሁ የኔ ጌታ
እራሴን ልየው ከጠዋት እስከማታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ