ስለ ማን?
Sele man
4:16 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቆይ ከአንተ ውጪ ስለማን ስለምን? ስለነማን? ላውራ?
አንደበቴን ስከፍት ስምህ ይቀናኛል
ፍቅርህ በልቤ ላይ እንደ አምድ ተተክሏል
ኢየሱስ(*2) ኢየሱስ ኢየሱስ እያልሽ ዘምሪ ያሰኘኛል
መፅሐፉ ተከፍቶ እስኪዘጋ ድረስ
ስላንተ ያወራል ድንቁ ጌታ ኢየሱስ
ነቢያት ሀዋርያት የመሰከሩልህ
መንፈስቅዱስ መጥቷል አንተኑ ሊገልጥህ
አብ አባትህ ብሏል 'የምወደው ልጄ'
አንተን አንተን ብልስ ነው ታድያ ወድጄ?
ቁጥር 2 · Verse 2
ሲነጋና ቀኑ ሲመሽ
ከእስትንፋስህ ከፊትህ እንዳልሸሽ
ፍቅርህ በዝቶ እኔን መውደድህ
አሸነፈኝ ከማን ላወደዳድርህ
አዝማች · Chorus
ኦሆሆሆ በቃ አልችልም ኦሆሆሆ ካንተ ልለይ
ኦሆሆሆ ደስ አይለኝም ኦሆሆሆ ፊትህን ሳላይ
ቁጥር 3 · Verse 3
( Choir )
ህይወት ሆኖልኛል የመአዛ ሽታ
አረ ማን ሊተካህ ሆኖ ባንተ ቦታ
ኑሮዬ ባንተ ላይ የተደገፈ ነው
ከእቅፍህ ቢያወጡኝ አቅሜ ምንድነው?
የአፍህ ቃል እኮ ነው የማዳንህ ስራ
ምህረትህን ያሳየኝ በራሴ እንዳልኮራ
እንዳንተ የሚሆን ስላጣሁ ፈልጌ
ሌላውን አልሰብክም እኔ አንተን ሸሽጌ
በጋ ክረምት ፀደይ በልጉ
በሀዘን ደስታ በክፉ በደጉ
በማለዳ በረፋዱ
ያዋጣኛል ስምህን መውደዱ
አዝማች · Chorus
ኦሆሆሆ በየቀኑ ኦሆሆሆ በየወሩ
ኦሆሆሆ ከአመት አመት ኦሆሆሆ አንተን ማለት
ኦሆሆሆ እኔ አልችልም ኦሆሆሆ ካንተ ልለይ
ኦሆሆሆ ደስ አይለኝም ፊትህን ሳላይ
ቁጥር 4 · Verse 4
ህይወት ሆኖልኛል የመአዛ ሽታ
አረ ማን ሊተካህ ሆኖ በአንተ ቦታ?
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ