አቤት ደግነት
Abiet Degenet
2016 · ትራክ 3 · 5:09 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እውነትነቱን በመስቀል ላይ
መቶ አለቃው ጌታዬን ቢያይ
ተንበረከከ ሰገደለት
ነካው የጌታ ቅንነት
እንኳን አሁን ከፍ ከፍ ብሎ
አሸንፎአል ተንጠልጥሎ
ሳያስፈራራ ሰው አንበርካኪ
እንደእርሱ የለም ፍቅር ሰባኪ
አዝማች · Chorus
አቤት ደግነት ቸርነቱ
ለሰው ያሳየው ምህረቱ (፮x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍቅር ምህረቱን የቀመሱቱ
ውበቱን ያዩ ሐዋሪያቱ
ስለእርሱ ኖረው መረጡ ሞት
ለፍቅሩ ሆኑ ሰማዕታት
ተነክተው በምህረቱ
ተነክተው በቸርነቱ
ነክቶአቸው ገርነቱ
ነክቶአቸው የዋህነቱ
የቱ ጀግና ነው እጁን ያልሰጠ
የሱስን አይቶ ያልደነገጠ
ልከተልህ ያላለ ማነው
የኢየሱስ ፍቅር አሸናፊ ነው
ከጫፍ ጫፍ ስንቱን ማረከ
በፍቅሩ አንበረከከ
ምን ዓይነት ፍቅር ነው እንጃ
ወደደንው/ሰገድን ያለ ጠመንጃ (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤት ትህትና አይ ቅንነት
ሰውን ያስተማረ ኖሮ በሕይወት
የሚሸጠውን እግር ያጠበ
ሩህሩህ ነው ጌታ ፍቅር ያነገበ
ይህንን ጌታ የምትወዱት
አስቲ ከእኔ ጋር ኢየሱስን እንዲህ በሉት (፪x)
እንዳንተ ያለ እንዳንተ ያለ
እንዳንተ ያለ ኧረ ማን አለ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ