ሁሉን ቀድሜዋለሁ
Hulun Qedemiewalehu
2016 · ትራክ 4 · 7:30 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ
የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ
የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ (፪x)
ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ
የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ጥበበኛዋ ሴት ቀዝቃዛውን ክረምት
ሩቅ አይታ ልብሷን ሰፋች መከራውን ቀደመች
እኔም እንደ እሷ ሁሉን ቀድምያለሁ
በእየሱስ ተደስቻለሁ (፪x)
ሃዘንን ቀድሜዋለው ጭንቀትን ቀድሜዋለው
ተድላን ቀድሜዋለው ስኬትን ቀድሜዋለው
አዝማች · Chorus
የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ
የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ
የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ (፪x)
ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ
የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ
ቁጥር 4 · Verse 4
የተቀደመ ነው የቀረው ዘመኔ
የዘላለም ደስታ ኢየሱስ ሆኖኝ ለእኔ
ቀድሜ ተደስቻለው (፪x)
በኢየሱስ ተደስቻለው (፪x)
እንደ ወንዝ ነው ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ከውስጤ
አይቋረጥም ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ከውስጤ
አዝማች · Chorus
የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ
የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ
የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ (፪x)
ነገር ቢሞላ ነገር ባይሞላ
የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ
ቁጥር 6 · Verse 6
ደስታ እና ሃዘኔ እኩያ ነበሩ
በልኬት ቁመና የሚፎካከሩ
ኢየሱስ ግን የሰጠኝ ደስታ
አይስተካከል ከሁኔታ
አባቴ የስጠኝ ደስታ
አይስተካከል ከሁኔታ
እንደ ወንዝ ነው ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ከውስጤ
እንደ ወንዝ ነው ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ከውስጤ
አዝማች · Chorus
የደስታዬ ምንጭ አንተ ነህ
ቁጥር 7 · Verse 7
አንተ ነህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ