ባለውለታዬ
Baleweletayie
2016 · ትራክ 8 · 6:40 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ወረቀት ብዕሬን አገናኘሁኝ
ስለጌታ ውለታ መጻፍ አሰኘኝ
የትኛውን ጽፌ የቱን ልተወው
የምለውን ባጣ እንዲህ ልበለው ልበለው
አዝማች · Chorus
ባለውለታዬ ነው ጌታዬ (፬x)
ውለታ አለብኝ የማልመልሰው
ቁጥር 2 · Verse 2
የእግዚአብሄር ልጅ ለእኔ የሰራው
ስለ ኢየሱስ ሰፊ ጊዜ ያሻኛል
እንኳን ቀኑ ዘላለም ያንሰኛል
ታሪክ የሌለውን ባለታሪክ
ጠላት የሆንኩት ወዳጅ አረክ
አሳዳጅ የሆንኩትን ነካኽኝና
በቅዱሳኑ ፊት አቆምከኝና
ቁጥር 3 · Verse 3
ዘምር አልከኝ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በስንኝ ቋጠሮ ችዪ ላልሰንቅ
ጠልቄ ባስብም አቅሜ እስኪያልቅ
አወይ በትንሿ በዚች ወረቀት
ጭሬ አልጨርሰው የሱን ሰጪነት ለጋስነት
መካኒቱ ሰባት ወለደች
ሳራም በእርጅና ጸነሰች
ሙሴን በጥበብ አሳደገ
ምስኪኑን ዳዊት ንጉሥ አደረገ
እንደዚህ ነው የኢየሱስ ስራ
አይጨረስ ሁሌም ቢወራ
እኔም አለኝ የምለው
አግኝቶኛል ውለታው
አዝማች · Chorus
ባለውለታዬ ነው ጌታዬ (፬x)
ውለታ አለብኝ የማልመልሰው
ቁጥር 5 · Verse 5
የእግዛብሄር ልጅ ለእኔ የሰራው
ስለ ኢየሱስ ሰፊ ጊዜ ያሻኛል
እንኳን ቀኑ ዘላለም ያንሰኛል
ብዙ ነው የሱ ውለታ
ሳስበው ጥዋት እና ማታ
ግርም ይለኛል ድንቅ ይለኛል ቃላት ያጥረኛል
በምን ቋንቋ ነው በምን አንደበት
የምገልጸው የሱን በጐነት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ