አቤቱ
Abietu
2020 · ትራክ 8 · 4:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምን አቃተህና ማህተሙን ፈትተሀል
ሰባቱን ጥቅል መጽሐፍ ልትከፍት ችለሀል
እንቆቅልሽ ፈቺ በማደሪያህ አለህ
በዙፋን ላይ ሆነህ ሁሉን ታድሳለህ
አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል
የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል
አዝማች · Chorus
በማደሪያህ ላይ አለህ/3
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ
በችሎትህ ላይ አለህ/3
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
አልፋና ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ
ጅማሬህ አይታወቅ ያንተ መጨረሻ
ገደብ ልክ የሌለህ ሀያል የእኛ ጌታ
በግርማ ሞገስህ ሁሉን የምትረታ
አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል
የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል
ቁጥር 3 · Verse 3
የሞትና የሲኦል መክፈቻ በእጅህ ነው
በላይ ቢሆንም በታች ስልጣን ያንተ ነው
አዶናዩ ጌታ ምንስ ይሳንሀል
ቋጠሮውን ልትፈታ ብቻህን ችለሀል
አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል
የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል
አዝማች · Chorus
በማደሪያህ ላይ አለህ/3
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ
በችሎትህ ላይ አለህ/3
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ
ቁጥር 4 · Verse 4
በረከት እና ክብር ጥበብም ምስጋና
ለታረደው በግ ይሁን ለዚያ ለገናና
ሰቃይን እና ችግር መከራን ያስረሳ
ኢየሱስ ብቻ ነው የይኁዳ አንበሳ
አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል
የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል
ቁጥር 5 · Verse 5
በማደሪያህ ላይ አለህ (፫x)
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ
በችሎትህ ላይ አለህ/3
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ