አልደራደርም
Alederaderem
2020 · ትራክ 5 · 3:36 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሃይማኖቴን እምነቴን/ማኅተሜን አንተን ጌታ
ከላይ ያኔ ያገኘሁህ የእኔን ቤዛ
ያምላኬን ፀጋ በመሴሰን አለውጥም
ንጉሤን አንተን ኢየሱሴን አልክድም (፪x)
አዝማች · Chorus
አልደራደርም በአንተ ጉዳይ
ቁጥር 2 · Verse 2
እንደ ቀልድ አላይም የሆንከውን መስቀል ላይ
ከአብ ዘንድ ያገኘሁህ ቅዱስ ስጦታ
አንተ ነህና የእኔ ጌታ
በመረቀልን በአዲሱና በሕያው መንገድ
ወደቅድስቲቱ በኢየሱስ ቀርበን
የእውነትን እቅቀት ካገኘን ወይ
ወደን ከሃጥያት እንዴት እንፀናለን
ወደን ሃጥያትን እንዴት እናደርጋለን
አዝማች · Chorus
አንደራደርም በአንተ ጉዳይ
ቁጥር 3 · Verse 3
እንደ ቀልድ አናይም የሆንከውን መስቀል ላይ
ከአብ ዘንድ ያገኘንህ ቅዱስ ስጦታ
አንተ ነህና የእኛ ቤዛ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ