ያልኖርከበት
Yalnorkebet
2020 · ትራክ 9 · 7:22 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያልኖርክበት ዘመን የለም
ካንተ በፊት ዘመን አልነበረም (*2)
ለዘላለምን ፈጥረህ
ለዘላለም ትኖራለህ (*2)
አዝማች · Chorus
ከምልህ በላይ ካልኩህም በላይ
ትልቅ ነህ ጌታ
ዘመን ዘምኖ ያልለወጠህ አንተ ነሀ
ከምልህ በላይ ካልኩህም በላይ
ትልቅ ነህ ጌታ
ዘመን ዘምኖ ያልቀየረህ አንተ ነሀ
ዘመን ዘምኖ ያልለወጠህ አንተ ነሀ
ዘመን ዘምኖ ያልቀየረህ አንተ ነሀ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘመንህ አይቆጠርም
አመታቶችህ አያልቁም
ለመንግስትህ ፍፃሜ የለውም
ዘመንህ አይቆጠርም
አመታቶችህ አያልቁም
ለመንግስትህ ፍፃሜ የለውም
ሁሉ ያረጃል ሁሉም ያልፋል
እንደ መጎናጸፊያ ይጠቀለላል
አንተነትህ ግን በምንም አይለወጥም
ጥንትም አሁንም ያለህ ዘላለማዊ ነህ
አዝማች · Chorus
ከምልህ በላይ ካልኩህም በላይ
ትልቅ ነህ ጌታ
ዘመን ዘምኖ ያልለወጠህ አንተ ነሀ
ከምልህ በላይ ካልኩህም በላይ
ትልቅ ነህ ጌታ
ዘመን ዘምኖ ያልቀየረህ አንተ ነሀ
ዘመን ዘምኖ ያልለወጠህ አንተ ነሀ
ዘመን ዘምኖ ያልቀየረህ አንተ ነሀ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከአማልክት መሀል አንዱ አይደለህም
ከጌቶች መሀል አንዱ አይደለህም
ከአባቶች መሀል አንዱ አይደለህም
የሁሉ የበላይ ትልቅ የሆንህ
ክብረህ ያለህ ማንም ሳይተካከልህ
የሁሉ የበላይ ሀያል የሆንህ
ነግሰህ ያለህ ማንም ሳይተካከልህ
ቁጥር 4 · Verse 4
የለም የለም እንዳንተ ያለ የለም (*2)
እንዳንተ ያለ የለም (*2)
የለም የለም እንዳንተ ያለ የለም (*2)
እንዳንተ ያለ የለም (*4)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ