Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተመርጫለው

Temerechalew

2020 · ትራክ 11 · 3:47 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተመርጫለው እኔ

ተወድጃለው እኔ

ፀድቄአለው በእርሱ

እንድኖርለት ለእርሱ (፪x)

ፀጋው በእምነት አድኖኝ

ኢየሱስ ጽድቁን አልብሶኝ

ስለኔ በአብ ፊት ታይቶ

ፈጽሞታል ሥራዬን ጨርሶ (፪x)

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ፀጋው አቁሞኛል

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ምህረቱ አኑሮኛል

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ቸርነቱ በዝቶልኛል

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ለዚህ ጌታ ክብር ይገባዋል

ለዚህ ጌታ ክብር ይገባዋል

ለዚህ ጌታ ስግደት ይገባዋል

ለዚህ ጌታ ልዕልና ይገባዋል

ለዚህ ጌታ አምልኮ ይገባዋል

ገና ከፍጥረት በቁጣ ነበርኩኝ

በበደሌ ምክንያት ሙት የሆንኩኝ

በኃጢአቴ መብዛት ሙት የሆንኩኝ (፪x)

ግን በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ

ከኢየሱስ ጋር ሕይወትን ለእኔ አደለ

ግን በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ

ከኢየሱስ ጋር ሕይወትን ለእኔ እንኪ አለ

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ፀጋው አቁሞኛል

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ምህረቱ አኑሮኛል

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ቸርነቱ በዝቶልኛል

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ለዚህ ጌታ ክብር ይገባዋል

ለዚህ ጌታ ክብር ይገባዋል

ለዚህ ጌታ ስግደት ይገባዋል

ለዚህ ጌታ ልዕልና ይገባዋል

ለዚህ ጌታ አምልኮ ይገባዋል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ