አቤቱ ውበትህን
Abietu Webetehen
2001 · ትራክ 2 · 5:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ታላቅነትህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (፪x)
አቤቱ ውበትህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (፪x)
ፊትህ እንደ ፀሐይ የሚያበራ
ድምጽህ ነጐድጓድ ነው የሚያስፈራ
ደረትህን በወርቅ የታጠቀ
እጅግ ያማረ ነው ውበትህ
አዝማች · Chorus
አቤቱ ውበትህ እያደነቀ
ቁጥር 2 · Verse 2
አቤቱ ሥራህን እያደነቀ
ታላቅነትህን እያደነቀ
ልቤ መልካም ነገርን ይኸው አፈለቀ (፪x)
እንደፈጣን ፀሓፊ አንደበቴን እከፍታለሁ
መቼ ያስችለኛል አምላኬ ክብርህን እያየሁ
አመሰግንሃለው አሃሃ አመሰግንሃለሁ (አመሰግንሃለው)
አመሰግንሃለው ኦሆሆ አመሰግንሃለሁ
የቤትህን ስርዓት አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (፪x)
አቤቱ ጥበብህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (፪x)
የቤትህን ስርዓት አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (፪x)
አቤቱ ጥበብህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (፪x)
ስለ አንተ ከሰማሁት ዝና ይልቅ
በዓይኔ የማየው ሆነብኝ ድንቅ
ስለዚህም ነፍሴ ተማረከች
የምሥጋናን ዜማ አፈለቀች
አዝማች · Chorus
አቤቱ ውበትህ (አቤቱ ውበትህ) እያደነቀ (እያደነቀ)
ቁጥር 3 · Verse 3
አቤቱ ሥራህን (አቤቱ ሥራህን) እያደነቀ (እያደነቀ)
ታላቅነትህን (ታላቅነትህን) እያደነቀ (እያደነቀ)
ልቤ መልካም ነገርን (ልቤ መልካም ነገርን)
ይኸው አፈለቀ (ይኸው አፈለቀ) (፪x)
እንደፈጣን ፀሓፊ አንደበቴን እከፍታለሁ
መቼ ያስችለኛል አምላኬ ክብርህን እያየሁ
አመሰግንሃለው አሃሃ አመሰግንሃለሁ (አመሰግንሃለው)
አመሰግንሃለው ኦሆሆ አመሰግንሃለሁ
የእጆችህን ሥራ አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (፪x)
አቤቱ ፍጥረታትን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (፪x)
ጨረቃና ፀሐይ ከዋክብት
በምድር ላይ ያሉ እንስሳት
ሁሉ በአንተ ለአንተ ተፈጥረዋል
አምላኬ ሆይ ሥራህ ያስደንቃል
አዝማች · Chorus
አቤቱ ውበትህን እያደነቀ
ቁጥር 4 · Verse 4
(አቤቱ ሥራህ) አቤቱ ሥራህ እያደነቀ
(ታላቅነትህን) ታላቅነትህን እያደነቀ
ልቤ መልካም ነገርን ይኸው አፈለቀ (፪x)
እንደፈጣን ፀሓፊ አንደበቴን እከፍታለሁ
መቼ ያስችለኛል አምላኬ ክብርህን እያየሁ
አመሰግንሃለው አሃሃ አመሰግንሃለሁ (አመሰግንሃለው)
አመሰግንሃለው ኦሆሆ አመሰግንሃለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ