የማዕረግ መዝሙር
Yemaereg Mezmur
2001 · ትራክ 6 · 6:21 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የማዕረግ መዝሙር እዘምራለሁ
ያከበርከኝን አንተን አከብራለሁ
ምሥጋናዬን ጌታ ተቀበለው
አምልኮዬን ኢየሱስ ተቀበለው (፪x)
በህብህ ምሥጋናህ ውስጥ ትኖራለህና
በህዝብህ አምልኮ ውስጥ ትገኛለህና
እኔም አመሰግንሃለሁ
ሌላ ሌላማ ምን እላለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤቱ በፈቃድህ ኃይልን ሰጥተኸኛል
በፊትህም ደስታ ደስ አሰኝተኸኛል
ክብሬ ዝምም እንዳትል ትዘምርልሃለች
ነፍሴም ያንተን ውለታ ለሁሉ ታወራለች
አዝማች · Chorus
የማዕረግ መዝሙር እዘምራለሁ
ያከበርከኝን አንተን አከብራለሁ
ምሥጋናዬን ጌታ ተቀበለው
አምልኮዬን ኢየሱስ ተቀበለው (፪x)
በህብህ ምሥጋናህ ውስጥ ትኖራለህና
በህዝብህ አምልኮ ውስጥ ትገኛለህና
እኔም አመሰግንሃለሁ
ሌላ ሌላማ ምን እላለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሰው ልጆች ሁሉ ፊት ለእኔ ያዘጋጀሃት
ለሚፈሩህም ደግሞ ሰውረህ ያስቀመጥካት
አቤቱ ቸርነትህ እጅግ በዝታልኛለች
የጽድቅንም ብድራት አዘጋጅታልኛለች
ክብር ለአንተ ብቻ ነው
ሞገስ ለአንተ ብቻ
ክብር ለአንተ ብቻ ነው
ሞገስ ለአንተ ብቻ
ለሌለህ አቻ ፤ ለሌለህ አቻ
ለሌለህ አቻ ፤ ለሌለህ አቻ (፪x)
የሌለህ ተወዳዳሪ ግርማህም እጅግ አስፈሪ
በሠማይና በምድር ታላቅ ነህ የእኛስ እግዚአብሔር
መለወጥ በአንተ ዘንድ የለም
ያው ነህ ለዘለዓለም
ያው ነህ ለዘለዓለም (፪x)
ክብር ለአንተ ብቻ ነው
ሞገስ ለአንተ ብቻ
ክብር ለአንተ ብቻ ነው
ሞገስ ለአንተ ብቻ
ለሌለህ አቻ ፤ ለሌለህ አቻ
ለሌለህ አቻ ፤ ለሌለህ አቻ (፪x)
ዝቅ ዝቅ ብዬ ከፍ አደርግሃለሁ
በምሥጋና ዜማ እቀኝልሃለሁ
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ብለሃልና
ላመስግንህ ዛሬ በአዲስ ምሥጋና (፪x)
ለታላቅነትህ ፍጻሜ የለህም (፫x)
ለኃያልነትህ ፍጽማኤ የለህም (፫x)
ለታላቅነትህ ፍጻሜ የለህም (፫x)
ለኃያልነትህ ፍጽማኤ የለህም (፫x)
ገናና ነህ ብቻህን ገናና ነህ
ገናና ነህ ብቻህን ገናና ነህ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ